አፕል ሲነሳ አብሮ የሚነሳው ስቲቨ ጆብስ ቢሆንም የመጀመርያዎቹን አፕል ኮምፕዩተሮች ፈጥሮ በእጁ የስራቸው ስቲቭ ዎዝኒያክ ነው።
እ.ኤ.አ በ1950 አሜሪካ ቨርጂኒያ ውስጥ የተወለደው ስቴፈን ጋሪይ ዎዝኒያክ “ዎዝ” በሚል ቅጽል ስሙ ይታወቃል።አባቱ በሚሳኤል እና ህዋ ሳይንስ ላይ በሚሰራ ድርጅት ወስጥ ኤሌክትሪካል ኢንጅነር የነበሩት ስቲቨ ዎዝኒያክ ለሂሳብና ኤሌክትሮኒክስ ትምህርቶች የተለየ ፍቅር ነበረው።ብዙዎች “የ ኮምፕዩተር አብዮት አባት” በማለት የሚጠሩት አሜሪካዊው ኤሌክትሮኒክስ ኢንጅነር ስቲቭ ዎዝኒያክ የመጀመርያዎቹን አፕል ኮምፕዩተሮች ዲዛይን ማድረግና ማምረት የእርሱ ሃላፊነት ነበር።
እ.ኤ.አ በ1971 ብሉ ቦክስ የተሰኘ የስልክን ኔትዎርክ ሰብሮ በመግባት ወደሩቅ ቦታዎች ያለክፍያ መደወል የመያስችል መሳርያ ሰርቷል።በዚህ ወቅት ነበር ከ ስቲቭ ጆብስ ጋር የተዋወቁት ።
እ.ኤ.አ በ1969 የመጀመርያ አመት ተማሪ እያለ በሚማርበት ኮሎራዶ ቦውልደርስ ዩኒቨርሲቲ የነበሩ የዩኒቨርሲቲውን ኮምፕዩተሮች ሃክ በማድረጉ ምክንያት ከኮሌጁ ተባረረ። የኮሌጅ ትምህርቱን ያቋረጠው ስቲቭ ዎዝኒያክ በተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ድርጅቶች ውስጥ የሰራ ሲሆን በ1975 HP (ሂውሌት ፓከርድ)ን ተቀላቅሎ የካልኩሌተር ዲዛይነር ሆኖ መስራት ጀመረ።
ሆምብሪው የተባለ የኮምፕዩተር ክለብ ውስጥ ይሳተፍ የነበረው ዎዝኒያክ እ.ኤ.አ በ1976 በ HP ወስጥ እየሰራ ባለበት ወቅት በጊዜው አዲስ የነበረውን ኢንቴል (intel 8080) ማይክሮፕሮሰሰርን ተጠቅሞ የራሱን ኮምፕዩተር ቢሰራም ድርጅቱ ግን ይህን ኮምፕዩተር ለማሳደግ ፍላጎት ሳያሳይ ቀረ።ስቲቭ ኮምፕዩተሮቹን ይሰራ የነበረው ሆምብሪው ኮምፕዩተር ክለብ ውስጥ የነበሩ ጓደኞቹን ለማስደነቅ እንጂ አምርቶ ለመሸጥ አስቦ አልነበረም።
በዚህ ወቅት ነበር በተመሳሳይ የሆምብሪው ኮምፕዩተር ክለብ አባል የነበረው ስቲቭ ጆብስ የ ስቲቭ ዎዝኒያክን ስራ በማየት አብሮ ለመስራት ፍላጎት ያደረበት በዛው አመትም አፕል ኮምፕዩተር ካምፓኒ ብለው ድርጅቱን መሰረቱ።ለስራ መነሻ የሚሆን ብር ለማግኘት ስቲቭ ጆብስ ቮልስዋገን መኪናውን አንዲሁም ስቲቭ ዎዝኒያክ ደግሞ በዛን ዘመን በቀላሉ የማይገኘውን ካልኩሌተሩን ለመሽጥ ተገደዋል።
ማምረቻ ቦታችውንም የስቲቭ ጆብስ ቤተሰብ የቤት ውስጥ ጋራዥን በማድረግ ነበር የኮምፕዩተር ቦርዶችን ማምረት የጀመሩት።
እ.ኤ.አ በ1976 የሰሩት የመጀመርያው አፕልI ኮምፕዩተር ቦርድ የቴሌቪዥን ስክሪንን የሚጠቀምና፣ፊደሎችን ስክሪን ላይ ማሳየት የቻለ እና ቀላል የኮምፕዩተር ፕሮግራሞችን መጻፍ የሚያስችል በታሪክ የመጀመርያው የቤት ውስጥ መገልገያ ኮምፕዩተር ሆነ። ከዚህ የኮምፕዩተር ቦርዶች ሽያጭ ጥሩ ሰለነበር ከቦርድ ይልቅ ሙሉ በሙሉ ራሱን የቻለ ማለትም ኪቦርድና ስክሪን ያለውን አፕልII ኮምፕዩተርን እ.ኤ.አ በ1977 አመረቱ።
ከመጀመርያው አፕል I ምርት ስኬት በኋላ ዲዛይን ያደረገው አፕል II የመጀመርያው ቀለሞችን ማሳየት የቻለ እና Basic የተሰኘውን የኮምፕዩተር ላንጉጅ የያዘ ነበር።በተጨማሪም በ 1978 ለዚሁ ኮምፕዩተር የ ፊሎፒ ዲስክ መቀበያ ዲዛይን ያደረገለት ሲሆን ይህም ቀድሞ የነበረውን የ ካሴት ቴፕ መቀበያ አስቀርቷል።
በስቲቭ ዎዝኒያክ ድንቅ የኢንጅነሪንግ ብቃትና በ ስቲቭ ጆብስ አርቆ አሳቢነት አማካኘነት የመጀመርያው ከመዝናኛ ያለፈ ጥቅም የሚሰጠውን ኮምፕዩተር ለአለም አስተዋወቁ።
ዳንኤል ኮትክ የተብለ አፕል ወስጥ የሰራ ግለሰብ ሲናገር “ስቲቭ ዎዝኒያክ የፈጠራ ሰው ነው ስቲቭ ጆብስ ደሞ የንግድ ሰው ነው” ሲል ገልጿችዋል።
ስቲቭ ዎዝኒያክ ለረጅም ሰአታት ቢሮ ውስጥ ቁጭ ብሎ ሰርክዩቶችን መስራት፣የሚሻሻሉበትን መንገድ መፈለግና መጠናቸው ትንሽ ሆኖ ብዙ ስራ መስራት የሚችሉ ማድረግ የሚወድ አይነት ሰው ሲሆን አፕል አሁን ላለበት ደረጃ የደረሰው በእርሱ ምርቶች ላይ ተመስርቶ ነው።
በ1977 ያስተዋወቁት አፕልII ኮምፕዩተር በአለማችን በብዛት ከተመረቱ ኮምፕዩተሮች አንዱ ለመሆን በቅቷል።
ለአፕልII ተጨማሪ አዳዲስ ሃርድዋርና ሶፍትዌር ዲዛይኖችን ሲሰራ የነበረው ስቲቭ ዎዝኒያክ እ.ኤ.አ በ1981 ምንም የአወሮፕላን አብራሪነት ሲልጠና ሳይኖረው የግል አውሮፕላኑ እያበረረ ከ አየር ማረፍያው ብዙም ሳይርቅ ተከሰከሰ በዚህ አደጋም ለ5 ሳምንት የቆየ የረጅም ጊዜን ማስታወስ ችሎታን (Traumatic amnesia) ህመም ተጋልጦ ነበር በኋላም የ አፕልII ጌም የማስታወስ ችሎታዬ እንዲመለስ ረድቶኛል ሲል ተናግሯል።
ከዚህ ሁሉ በኋላ ወደ በርክሌይ ዩኒቨርሲቲ ተመልሶ ዲግሪውን ለማጠናቀቅ ቢሞክርም በድጋሚ ለማቋረጥ ተገዷል። በኋላም አፕል ለስራው እውቅና የሰጠው ሲሆን እ.ኤ.አ በ1987 ዩኒቨርሲቲው የኤሌክትሪካል ኢንጅነሪንግ ዲግሪ አበርክቶለታል።
እ.ኤ.አ ከ1979 እሰከ 1981 የነበረው የ አፕል ማኪንቶሽ ኮምፕዩተር ፕሮጀክት ባለቤት ስቲቭ ዎዝኒያክ ቢሆንም ከአውሮፕላን አደጋው በኋላ ቶሎ ወደ ሰራው መመለስ ባለመቻሉ ስቲቭ ጆብስ ፕሮጀክቱን እንዲመራው ሆኗል።
ከአፕልII በኋላ የተመረተው አፕልIII ግን በገበያ ላይ ስኬታማ ሳይሆን ቀረ በ1984 ምርቱ እንዲቋረጥ ተደረገ።ስቲቭ ዎዝኒያክ ሲናገርም “ አፕል III ሰኬታማ ያልሆነው ኮምፕዩተሩ ዲዛይን የተደረገው በሽያጭ ክፍሉ ስለሆነ ነው ።ማለትም የአፕልIII ሃሳብ የተጠነሰሰው ለገበያ ትርፍ እንጂን እንደ ከዚህ ቀደሞችሁ አፕሎች ሞያዊ/ኢንጅነሪንግ ነክ የሆነ መነሻ ሰላልነበረው ነው” ብሏል።
እ.ኤ.አ በ1987 ስቲቭ ዎዝኒያክ CL9 የተባለ የመጀመርያ የሆነ ፕሮግራም መደረግ የሚቸል ለሁሉም ተሌቪዥን የሚሆን(ዩኒቨርሳል) ሪሞት ኮንትሮል ሰርቶም ነበር።
ከ አውሮፕላን አደጋው በኋላ እ.ኤ.አ በ1982 ወደ አፕል ስራው የተመለሰው ስቲቭ ዎዝኒያክ የአስተዳደራዊ ስራ መስራትን ወደጎን በማለት የድርጅቱ ኢንጅነር ሆኖ 50ዶላር በወር እየተከፈለው መስራትን መረጠ(ይህ ክፍያ እስካሁን እየተከፈለኝ ነው ሲል እ.ኤ.አ በ2006 ባወጣው የህይወት ታሪክ መጽሃፉ ላይ አስፍሯል) ቢሆንም በ 1985 ይህንን ሰራውን አቁሟል።በዚህ ጊዜ ነበር ክስቲቭ ጆብስ ጋር በመሆን ናሽናል ሜዳል ኦፍ ቴክኖሎጂ የተሰኘ የክብር ሜዳልያን በወቅቱ የ አሜሪካ ፕሬዝዳንት ከነበሩት ሮናልድ ሬገን የተቀበለው።
ሰራውን ካቆመ 1985 ጀምሮ እስክ 2019 ድረስ የ አፕል የክብር አባል ሆኖም ቆይቷል።ስቲቭ ዎዝኒያክ በተደጋጋሚ በቃለ መጠይቆች ላይ ሲናገር “ ህልሜ ብዙ ብር ማግኘት ሳይሆን አሪፍ ኮምፕዩተር መስራት ነበር “ ይላል።
የስቲቭ ዎዝኒያክ አፕልን መልቀቅ
ከ አስተዳደራዊ ስራ ይልቅ የኢንጅነሪንግ ስራን ይወድ የነበረው ስቲቭ ዎዝኒያክ ሲናገር “አፕል ድርጅት እኔ መሆን የምፈልገውን እንዳልሆን እያደናቀፈኝ ነው ። አፕልን ስንመሰርት የነበሩት ጊዜያት ይናፍቁኛል አሁን ድርጅቱ እኔን የሚፈልገኝ አይመስለኝም ላለፉት 5 አመታት በተሳሳተ መንገድ እየሄደ ነው ‘’ ብሏል ።እ.ኤ.አ በ1985 የራሱን ድርሻ በመሸጥ አፕልን ለቋል።
በተጨማሪም ስቲቭ ዎዝኒያክ የድርጅቱ ምርቶች ግልጽ ፣ቀላልና የኮምፕዩተሮቹ ዲዛይኖች ሳይቀር ገሃድ ወጥተው ተጠቃሚዎች እጅ እንዲገቡ ፣ እንደፈለጉ እንዲጠቀሙበትና ካሰኛቸወም እንዲያሻሽሏቸው ያስብ የነበረና ከስቲቭ ጆብስ ኮምፕዩተሮች ድብቅ፣ሚስጥራዊ እና የተገደቡ የማድረግ ሃሳብ ጋር እንዳልተግባቡ ይነገራል።
ስቲቭ ዎዝኒያክ አፕልII ዲዛይን ሲደረግ 8 ከሌሎች መገልገያዎች ጋር ኮምፕዩተሩን የሚያገናኙ ስሎቶች እንዲኖሩት ቢያስብም ስቲቭ ጆብስ ግን 2 ስሎቶች (ለ ፕሪንተርና ሞደም ማገናኛ )ብቻ ይበቃል በማለቱ ብዙ የተከራከሩ ቢሆንም በመጨረሻም 8 ስሎቶች እንዲኖሩት ተሰማምተዋል።
ስቲቭ ዎዝኒያክ ሲናገርም “ስቲቭ ጆብስ ነገሮችን ዝግ እና ድብቅ ማድረግ ይወዳል።ድርጅቱን በአፕልII ስንጀመር ሁሉም ነገሮች ለሰዎች ክፍት ነበሩ ተጠቃሚዎች በፈለጉት መልኩ እንዲያሻሽሉትና እንዲጠቀሙበት ዲዛይኖቹንና ንድፎቹን በሙሉ አጋርተናል ስለዚህ እኔም የ Open source (ዲዛይንና ንድፍን ያለገደብ ለሰዎች ማጋራት) አስተሳሰብን አራምዳለው “ ብሏል።
ስቲቭ ዎዝኒያክ አፕልን ከለቀቀ በኋላ በጥቂቱ
ስቲቭ ዎዝኒያክ አፕልን ከለቀቅ በኋላ እ.ኤ.አ በ 1987 CL9 የተባለ የመጀመርያ የሆነ ፕሮግራም መደረግ የሚቸል ለሁሉም ተሌቪዥን የሚሆን (ዩኒቨርሳል) ሪሞት ኮንትሮል ስርቶ ለገብያ አቅረቦ ነበር።እንዲሁም በሚወደው ህጻናትን ኮምፕዩተር በማስተማሩም ቀጥሏል።እ.ኤ.አ በ2001 ደግሞ WOZ የተሰኝ በ ገመድ አልባ ቴክኖሎጂ ላይ የሚሰራ ድርጅት አቋቁሟል ነገር ግን በ 2006 WOZ ሲዘጋ እንደገና አኪኮር የተስኘ የቴክኖሎጂ ድርጅቶችን በማሳደግ ላይ የሚሰራ ደርጅት አቋቁሟል።
በመቀጠልም እ.ኤ.አ ከ2009 እስከ 2014 ድረስ fusion io በተባለ ድርጅት በ ቺፍ ኢንጅነርነት አገልግሏል።በ2017 ደግሞ WOZU የተባለ የ ኦንላይን ማስተማርያ መስርቷል።
ስቲቭ ዎዝኒያክ ባልደረባው እና ጓደኛው የነበረው የስቲቭ ጆብስ ሂውት እስካለፈበት 2011 ድረስ የነበራቸውን ቅርበት አላቋረጠም ነበር።
ስቲቭ ዎዝኒያክ በቅርቡም በፈረንጆቹ ሴፕቴምበር ወር 2021 ላይ እንዳሳወቀው ከሌሎች አጋሮቹ ጋር በመሆን ፕሪቫተር ስፔስ የተሰኘ በህዋ ላይ የሚገኙ የ መንኩራኩር ፊርስራሾችነ ና ሌሎች ሰው ሰራሽ የህዋ ቆሻሻዎችን ( space debris) በማጽዳት ላይ ያተኮረ ድርጅት መስርተዋል።
በተጨማሪም iWOZ በሚል ርእስ የሂዎት ታሪኩን የያዘ መጽሃፍ እ.ኤ.አ በ 2006 ለንባብ አብቀቷል።
ለ ስቲቭ ዎዝኒያክ የተሰጡ እውቅናዎች
የተለያዩ 4 ፓተንቶች ያገኘው ስቲቭ ዎዝኒያክ የ ኮምፑተር ስክሪኖች ከ ጥቁርና ነጭ ሳይገደቡ ሁሉንም ቀለሞች ማሳየት እንዲችሉ ያደረገበት ፈጠራው ታዋቂ ነው። ለኮምፕዩተር ዘርፍ እንዲሁም በበጎ አድራጎት ላበረከተው አስተዋጽኦ የተለያዩ 14 የሚሆኑ እውቅና እና ሽልማቶች አግኝቷል።በተጨማሪም ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች 10 የክብር ዲግሪዎች ተሰጥተውታል።
እንዲሁም አፕልን በመወከል የተለያዩ ግብዣዎች ላይ ይካፈላል ይህም በአመት እስከ 120000 ዶላር ያስገኘለት እንደነበር ይገመታል።
የስቲቭ ዎዝኒያክ የእጅ ሰዓት
ስቲቭ ዎዝኒያክ ከግራ እጁ የማትለየው ከ45 ዓመት በላይ ያስቆጠረች ኒክሲ (Nixie) የተሰኘች የእጅ ሰዓት አለችው።ይቺ ስዓት በቫክዩም ትፑብ ቴክኖሎጂ (በጋዝ የተሞሉ ትንንሽ ብርጭቆዎች በሚፈጥሩት ብርሃን ቁጥር የሚጽፍ) የምትሰራና ከፈተኛ ሃይል የምትጠቀም ሰዓት ነች።
በ2015 ስለ ሰዓቷ ሲናግርም “ ምርጥ ሰዓት ነው። ያልተለመዱ ነገሮችን እወዳለው። በ ቫክዩም ትዩብ የሚሰሩ ሰዓቶች ምርት ለ 45 አመት ቆሞ ነበር ።ይህ ስዓት ውሃ ውስጥ ቢገባም ምንም አይሆንም ነገር ግን ባትሪውን በደቂቃዎች ውስጥ ይጨርሳል ምክንያቱም ይህ አፕል ዋች አይደለም “ ብሏል።
የ Right to repair ንቅናቄ
አሁን 71ኛ አመት እድሜው ላይ የሚገኘው ስቲቭ ዎዝኒያክ ከብዙ የ ቴክኖሎጂ ድርጅቶች ተቃውሞ እየገጠመው ቢሆንም በ2021 Right to repair (የገዙትን እቃ የመጠገን መብት) የሚል ንቅናቄን ተቀላቅሏል።ይህም ሰዎች የገዙትን የኤሌክትሮኒክስ እቃ መጠገን የሚያስችላቸውን መረጃና የሚቀየሩ እቃዎችን ያለገደብ የማግኘት መብት የሚስጥ ህግ እንዲወጣ የሚጠይቅ ንቅናቄ ነው ።
ስቲቭ ዎዝኒያክ በንግግሩም “እኔ ቴክኖሎጂ ግልጽ ፣ለሁሉም ክፍት እና ነጻ በነበረበት ጊዜ ባላድግ ኖሮ አፕልን ዛሬ አናየውም ነበር” ብሏል።
ነገር ግን የዚህ ሃሳብ ተቃራኒ ሆኖ ብቅ ያለው አፕል “የመጠገን ፍቃዴን የምሰጠው ለተፈቀደላቸው ቴክኒሽያኖች ብቻ ነው ። እንዲሁም የሚቀየሩ እቃዎችና የ ጥገና መረጃዎችን ለሁሉም ክፍት አላደርግም” ብሏል።
Keep the good work up brother. Thank you in advance