
ሮቦቶችን ለብዙ ጊዜ ህክምና ላይ፣ሰውን ማዝነናናት ላይ እንዲሁም ፋብሪካ ውስጥ ማየት የተለመደ ከሆነ ሰነባብቷል።ቢቢሲ ደግሞ ያገሬውን ሰዎች ለ ክሪስማሳቸው ምግብ የሚያዘጋጅላችሁ ሼፍ ሮቦት ይኼውላችሁ እያለ ነው። በርግጥም ይሄ ዜና በተሰራበት ሰዓት ፈረንሳይ ውስጥ ሁለት የሮቦቲክ ኢንጂነሪንግ ተማሪ የሆኑ ልጆች ከሁለት ቅርጫፍ በላይ ያለው በሮቦት የሚታገዝ “ፓዚ” የሚባል ፒዛ ቤት ከፍተው እየሰሩ ይገኛሉ።

እንድ የሰው ሰራተኛ ብቻ ቀጥሮ፣እሱም ለማስተናገድና ፒዛ ውስጥ የሚገቡትን ንጥረ ነገሮች ለሮቦቱ የሚጨምር ሲሆን ከዛ ውጪ ያሉትን ስራዎች ግን ሮቦቱ እያከናወነ ለደንበኞቻቸው ፒዛ በ 5 ደቂቃ ውስጥ እያበሉ ይገኛሉ።
ነገር ግን ቢቢሲ እንደሚለው ከሆነ በሚቀጥለው አመ ት “በሞሊ ሮቦቲክ ኪችን”የሚወጣው አዲሱ የሮቦት ሼፍ ከ 5000 በላይ የምግብ ረሲፒዎችን የሚሰራ አሰራሩን ሼፍ አንደርሰን ከተባለ በ2011 የቢቢሲ ማስተር ሼፍ ተሸላሚ ከሆነ ባለሙያ እጅ አጣጣል ሳይቀር ኮፒ ያደረገ ሼፍ ነው።
የሚያሳዝነው የአንድ ምግብ ዋጋ መካከለኛ ገቢ ያለው እንግሊዛዊ ይቅርና መለስተኛ ሀብታም እንኳን ሊቀምሰው የማይችል የዋጋ ክምር መሆኑ ነው።ትንሹ ዋጋ 150,000 ፓውንድ ነው።ይህን በተመለከተም የምግብ ቁጥጥር አማካሪ ባለሙያዋ ጁሊያ ሴይጋል እንዲህ አይነት ዋጋዎች መነሻ እንጂ ሮቦቶቹ በብዛት እየተመረቱ ሲሄዱ እንደሚቀንሱ ያላቸውን ምልከታ ተናግረዋል።
እንዲህ አይነት የምርምር ውጤቶች በሰው ሊመጡ ና ሊተላለፉ የሚችሉ በሸታዎችንናተዋሲዎችን በመቀነስ፤ አንድ ሰው አንድ ምግብ ለመስራት ይወስድ የነበረውን ጊዜ በማሳነስ ለደንበኛ እርካታን ቢያጎናፅፉም፤ ነገር ግን አሁን ላይ ያለውን የስራ አጥነት ችግር ከእጥፍም በላይ በማባባስ ለሰራተኛና ስራ ፈላጊ ግን ራስ ምታትን ያከናንባሉ።