40 ሺህ ዛፎችን የሚተክለው ድሮን ኤር ሲድ የተሰኘው የአውስትራሊያ የባዮቴክ ኩባንያ እነዚህ ራሳቸውን ችለው የሚበሩ ድሮኖች ከአየር ላይ በቀን ከ40,000 በላይ የዘር ፍሬዎችን በመትከል የደን ጭፍጨፋን መቋቋም እንደሚችሉ ተናግሯል።
የኤር ሲድ ቴክኖሎጂስ የደን መጨፍጨፍን ለመዋጋት አዲስ መንገድ ቀይሷል፡ አዳዲስ ዛፎችን ለመትከል ራሱን የቻለ የኢኮ-ድሮን ይዞ ብቅ ብሏል። በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የሚንቀሳቀሱት እና ራሳቸውን ችለው የሚሰሩት ድሮኖች ከሰማይ ላይ ወደ መሬት የሚተኮሱ ልዩ የዘር ፍሬዎች የተጫኑ ናቸው ሲል ዩሮ ኒውስ ዘግቧል።
የኤር ሲድ ቴክኖሎጂ መስራች አንድሪው ዎከር እንደዚህ ሲል ተናግሯል “እያንዳንዱ ሰው አልባ ድሮኖች በቀን ከ40,000 በላይ የዘር ፍሬዎችን መትከል ይችላሉ። ከተለምዷዊ ዘዴዎች ጋር ሲነጻጸር ይህ 25 እጥፍ ፈጣን እና 80% ርካሽ ነው።’’ ድሮኑ የዛፍ ዘሮችን ከሰማይ ላይ ወደ ምድር በመተኮስ እንዲተከል ያደርጋል የተባለ ሲሆን፤ ይህ የድሮን ቴክኖሎጂ በዓመት በሚሊየን የሚቆጠሩ ዛፎችን ለመትከል የሚያስችል ነው ተብሏል።

ድሮኖቹ በየቀኑ የዘር ፍሬ ለመትከል ከመውጣታቸው በፊት ከሚበሩበት አካባቢ ጋር የሚጣጣሙ የዘር ፍሬዎች ይጫናሉ። እንደ እውነቱ ከሆነ፣ እነዚህ እንክብሎች ከቆሻሻ ባዮማስ የተሠሩ በመሆናቸው፣ ወፎች ወይም ነፍሳት ወደ ዘሩ እንዳይደርሱ ስለሚከላከሉ ለሥነ-ምህዳር ተስማሚ ናቸው። ድሮኑን ዲዛይን ያደረገው የአውስትራሊያው ኤርሲድ ኩባንያ፤ ዘር ጣዩ ድሮን በቀን እስከ 40 ሺህ ዛፎችን መትከል የሚችል መሆኑን አስታውቋል።
ድሮኑ ዘሩን ከተለያዩ የዱር አራዊት ዓይነቶች ይጠብቃል፣ ዘሩ ከበቀለ በኋላ ይደግፋል እና ሁሉንም የሚፈልጓቸውን ንጥረ ነገሮች እና ማዕድናት ያቀርባል፤ አንዳንድ ፕሮባዮቲክስ በመስጠት የመጀመሪያ ደረጃ እድገትን ያፋጥናል። በቴክኖሎጂውን በመጠቀምም እስካሁን በአውስትራሊያ፣ በካናዳ እና በደቡብ አፍሪካ ከ50 ሺህ በላይ ዛፎችን መትከል መቻሉንም ኩባያው አስታውቋል።

በከባቢ አየር ውስጥ ያለውን የካርቦን ዳይኦክሳይድ መጠን ለመቀነስ እና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስ ይህ የደን መልሶ ማልማት ጥረት “ለሚቀጥለው ትውልድ የተመቻቸ እና ጥሩ አየር ያላት ምድርን ለመፍጠር መደረግ ያለበት ነው በማለት ዎከር ተናግሯል። የኤር ሲድ ቴክኖሎጂዎች በፈረንጆቹ 2024 እስከ 100 ሚሊዮን አዳዲስ ዛፎችን የመትከል አስደናቂ ግቡ ላይ እንደሚደርስ እርግጠኛ ናቸው።