አርቴፊሻል ጸሃይ ያስባለው እውነተኛዋ ጸሃያችን ላይ የሚካሄደውን nuclear fusion (ኒኩለሶችን በሃይል ማጣመር) በመኮረጅ ምድር ላይ ይህንን ሂደት በሳይንስ ላብራቶሪ ውስጥ በመስራት ከፍተኛ ሙቀት መፍጠር በመቻሉ ነው።
አርቴፊሻል ጸሃይ በመባል የሚጠራው በኒውክሌር የሚሰራ ከፍተኛ ሙቀት ያለው የሃይል ማመንጫ ማሽን (reactor) ሲሆን ይህም የሃይድሮጅን አተሞችን በማጋጨት የሚሰራ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ (reactor) እንጂ ራሱን የቻለ እንደምንሞቃት ጸሃይ የኳስ ቅርጽ ያለው ፣ የሚንቀለቀል እሳት የሚተፋና የሚበራ አካል ማለት አይደለም።
ይህ አርቴፊሻል ጸሃይ ተብሎ የሚጠራው የሃይል ማመንጫ ማሽን (reactor) ትክክለኛ ስሙ Experimental Advanced Superconducting Tokamak (EAST) ሲሆን ከአስርት አመት በላይ ምርምር ሲደረግበት የነበረና 1 ትሪሊዮን ዶላር ወጪ የፈጀ ነው። የዚህ EAST የተሰኘ የሃይል ማመንጫ የኳስ ቀርጽ ያለው ሳይሆን ከብዙ የሳይንስ እቃዎች ተገጣጥሞ ምድር ላይ የተሰራ የዶናት ቅርጽ ያለው በኒውኩሌር የሚሰራ ሃይል ማመንጫ (Nuclear fusion reactor) ነው።
EAST በሃገረ ቻይና ሄይፌይ ግዛት የሚገኝ ሲሆን በፈረንሳይ ሃገር የሚገኘውና 35 ሃገራት የሚሳተፉበት የግዙፉ ITER (International Thermonuclear Experimental Reactor) ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አንዱ አካል ነው ።
ITER በፈረንጆቹ 2035 የቴርሞ ኒውክሌር ሃይል ማመንጨትን ያነገበ ሲሆን የቻይናው EAST ሃይል ማመንጫ አዲስ ያገኘው ውጤት ለ ITER ግብዓት ይሆነዋል ተብሏል።
የቻይናው አርቴፊሻል ጸሃይ (EAST) በፈረንጆቹ 2021 ላይ 120 ሚልዮን ዲግሪ ሴሊሽየስ ይሚድርስ ሙቀትን ለ101 ሰክንዶች ብቻ ለቆየ ጊዜ መፈጠር ችሎ የነበረ ሲሆን ሰሞኑን ደግሞ 70ሚልዮን ዲግሪ ሴሊሽየስ ሙቀትን ፈጥሮ ለ 17 ደቂቃ ያክል አቆይቶ ነበር ይህም እስካሁን በ ፍዩዥን ሪአክተር (Fusion reactor ) ታሪክ ለረጅም ደቂቃውች የቆየ ሙቀት በመሆን ክብረወሰን ሆኗል።
ቻይና መፍጠር የቻለችው ይህ ሙቀት ከጸሃይ ሙቀት በ 5 እጥፍ የበለጠ ሲሆን ሪአክተሩ አርቴፊሻል ጸሃይ ያሚል ሰያሜን ያገኘው ለዚህ ነው።
አርቴፊሻል ጸሃይ (nuclear fusion) እንዴት ይሰራል?
አርቴፊሻል ጸሃይ (nuclear fusion) የሚፈጠረው ሁለት ትናንሽ ኒውክላዮች (nuclei) ተጋጨተው በመጣመር አንድ ትልቅ ኒኩለስ (nucleus) ሲፈጥሩ ነው።
ይህ ፍዩዥን በተፈጥሮም ጸሃይና ሌሎች ኮኮቦች ላይ የሚካሄድ ሲሆን በዚህም ሁለት የሃይድሮጅን ኒውክላዮች (nuclei) በከፍተኛ ሙቀትና ግፊት ተጋጨተው ሲጣመሩ ( fusion ሲፈጥሩ ) ክነዚህ ኒውክላዮች መጠኑ ያነሰ አዲስ ኒኩለስ (nucleus) የፈጠራል ። አዲሱ ኒኩለስ ከተጋጩት ኑኩላዮች መጠኑ ያነሰ ሆኖ ሰለሚፈጠር የተረፈው ከፋይ ሃይል ይሆናል ይህም በአልበርት አንስታይን ቀመር (E=mc2 ) የሚሰራና ኢነርጂ (E) እና ክብደት (m) እርስ በእርስ አንዱ አንዱን መፍጠር እንደሚችል ያሳያሉ።
ከላይ በጠቀስነው ሂደት ጸሃይና ኮኮቦች ብርሃነና ሙቀት መፍጠር የቻሉት።ይህ ቅንጣት አተሞችን በማጋጨት ሃይልን የማመንጨት ዘዴ ሃንስ ቤትሄ በተባለ ግለሰብ በ ፈረንጆቹ 1930 ላይ የተገኘ ግኝት ነው።
35 ሃገሮች የሚሳተፉበት ይህን ከጠፈጥሮ የተኮረጀ በሳይንስ ቤተ ሙከራ ውስጥ የሚሰራ ማለትም ቅንጣት አተሞችን በማጋጨት ከፈተኛ ሙቀትን ማማንጨትና ይህንንም ሙቀት ወደ ኤሌክትሪክ ሃይል በመቀየር ከብክለት የጸዳ (clean energy ) ሃይል በማመንጨት ለረጅም ዘመናት የሚያገለግል ማድረግን አላማው አድርጓል።
የቻይና ክብረወሰን
ቻይና በዚህ ሰሞን የሰበረችው ሪክርድ በአርቲፊሻል ጸሃይዋ (fusion reactor ) ለ17 ደቂቃ ያህል 70ሚልዮን ዲግሪ ሴሊሽየስ የሆነ ሙቀትን መፍጠር በመቻሏ ሲሆን ከእውነተኛዋ ጸሃይ መሃል (core) ላይ ያለው ሙቀት 15 ሚልዮን ዲግሪ ሴሊሽየስ ብቻ ከመሆኑ አንጻር አለምን አስደንቋል።
አርቴፊሻል ጸሃይ ያስባለው እውነተኛዋ ጸሃያችን ላይ ከሚካሄደውን nuclear fusion (ኒኩለሶችን በሃይል ማጣመር) በመኮረጅ ምድር ላይ ይህንን ሂደት በሳይንስ ላብራቶሪ ውስጥ ለመስራት በመቻሉ ነው።
ቻይና ከዚህ ቀደም በ EAST ላብራቶሪ ውስጥ 120 ሚልዮን ዲግሪ ሴሊሽየስ የሚበልጥ ሙቀትን መፍጠር ችላ የነብረ ቢሆንም ይህ ሙቀት የቆየው ግን ለ101 ሰከንዶች ብቻ ነበር።
በተጨማሪም የዚህ የችይና ሃይል ማመንጫ ፈተና ይሆናል የተባለው ሙቀቱን ከ100 ሚልዮን ዲግሪ ሴሊሽየስ በላይ ማድረግና ለረጅም ጊዜያት ሙቀቱ ሳይቋረጥ እንዲቆይ ማድረግ ነው።
የ ፍዩዥን ሃይል ማመንጫ “ultimate energy “ ወይም የመጨረሻው ትልቅ ሃይል ምንጭ የሚባልና አካባቢን የሚጎዳ ካርቦን የማያመነጭ ነው ይህም የሆነው አተሞችን ለማጋጨት የምንጠቀምባቸው ሃይድሮጅን እና ድዩትሪየም ጋዞች ንጹህ የሆኑን ጥቂት ተረፈ ምርት ያላቸው ሲሆኑ በምድረም ላይ እንደልብ ይገኛሉ።
ሰለ ቻይና አርቴፊሻል ጸሃይ የተሰራጩ ሃሰተኛ መረጃዎች
ባለፈው ሳምንት ትዊተር ላይ የተለቀቁ ምስሎች እና ቪድዮዎች “ ቻይና ምድር ላይ የራሷን ጸሃይ ሰርታ ወደ ህዋ አስወነጨፈች “ የሚል መልዕክት የያዙ ሲሆኑ ብዙዎች እውነት ነው ብለው ተቀባብለውታል።
ይህ ምስል ትዊተር ላይ 5000 ሰዎች ያህል ሪትዊት ያደረጉት ሲሆን በምስሉ ላይ ሰዎች ተሰብስበው አርቴፊሻል ጸሃይ ወደ ሰማይ ሲላክ የሚያሳይ ሲሆን በሚወነጨፍም ሰዓት ከፍተኛ ብርሃን ቦታው ላይ ሲፈጠር ይታያል።
ከምስሎቹም እስር “ አዎ ቻይናዊ ነች የሆነውም 100% እውነት ነው “ የሚልና “ አዲሱ ጸሃይ ደስተላለች ከነባሯ ጸሃያችን የበለጠች ደማቅና ቀለሟም ቢጫ ነው “ ይሚሉ ኮሜንቶች ተነበዋል።ምንም እንኳን ይህ ምስል የሌላ የህዋ ተልእኮ ምስል ቢሆንም ቻይና ግንአርቴፊሻል ጸሃይ በተባለው ሪአክተሯ ከእውነተኛዋ ጸሃይ 5 እጥፍ የበለጠ ሙቀትን መፍጠር ቸላለች።
የቻይና አርቴፊሻል ጸሃይ መቼ ሙሉ በሙሉ ሃይል ማመንጨት የጀምራል??
የቻይናው የሄይፌይ ኢንስቲትዩት ኦፍ ፊዚክስ ዳይሬክተር የሆኑት ሶንግ ያንታኦ እንደተናገሩት “ በሚቀጥሉት 5 አመታት ዋናውን የኒውክሌር ሃይል ማመንጫውን መገንባት እንጀመራለን ይህም ተጨማሪ 10 አመት ሊፈጅብን ይችላል። በፈረንጆቹ 2040 ላይ ግንባታው ተጠናቆ ሃይል ማመንጨት ይጀምራል” ብለዋል።
የማመንጫውን ሙቀት 100 ሚልዮን ዲግሪ ሴሊሽየስ ማድረስና ለረጅም አመታት እንዲቆይ ማድረግ ቀጣይ የጃይናው አርቴፊሻል ጸሃይ ፈተናዎች መሆናቸው አይቀርም።