ይሄ፡ ሳምንት የክሪስማስ ሳምንት በመሆኑ፣የክሪስማስ በዓል ደግሞ ከሌሎቹ በዓሎች ለየት የሚያረገው የስጦታ በዓል መሆኑ ነው።ታዲያ ይሄ ክፍተትም ለአጭበርባሪዎች ጥሩ አጋጣሚ ሆኖላቸዋል። አለም በቴክኖሎጂ እያደገች በመሞጣቷ የሌብነቱም ደረጃ እንዲሁ እየረቀቀ ና እያደገ መጥቷል።”ማን በድሮ በሬ ያርሳል” ያሉትም ሰውን ሲያወዛግቡና ሲያጭበረብሩ ብዙ ታይተዋል።ነገር ግን በዚህ ሳምንት ከዚህ በታች እንደተዘረዘሩት እንደ አምስቱ ባተሌ የነበረ የለም።
1.At&t የስጦታ መልዕክት
ይህ መልዕክት ሲጀምር ‘ የህዳር ወር ቢልህን ባግባቡ ስለከፈልክ ምስጋና ይገባሃልና ይቺን ስጦታ ተቀበለን’ በማለት ነው።
ከዚያም የክሬዲት ካርድ ቁጥር የሚጠይቅ አንድ የሽልማት ፎርም ያስሞላሉ።ሽልማቱም ስማርት ወች ነው በማለት። ከቶም ሽልማት¡¡¡¡
2. freeman paypal
ፍሪማን የታወቀ የልብስ ሻጭ ኩባንያ ነው። ታዲያ ከዚህ ኩባንያ ልክ እንዳዘዙ ሁሉ የሆነ ዕቃ ተልኮሎታል የሚል መልዕክት ይደርሶታል። የላኩሎትን ሊንክ እንደነኩም የ ፔይፓል አካውንቶን ያስገቡ ይላል ፣ተሽቀዳድመው ካስገቡላቸው፣ እዚህ ላይ ነው ቀለበታቸው ውስጥ የሚገቡት።
3. iphone 13 servey gift
በiphone ስም የሚጭበረበሩት ነገሮቾ ሁሌም ቢሆን ብዛታቸው የትየለሌ ነው። በዚህ ሳምንትም ‘እንዳያመልጦት!በነፃ የ iphone 13 ወረፋ ይያዙ’ የሚል መልዕክት መድረሱ ታዲያ የተለመደ ሆኗል።
- trust wallate security alert
ስለ አካውንትህ አደጋ ላይ መውደቅና ማስጠንቀቂያ በተለያዩ ታዋቂ ባንኮች ስም መልዕክት ይልካሉ ፣የይለፍ ኢንፎርሜሽን ደግሞ ካንተ ይቀበላሉ።
5. benz the lottery email
ከታዋቂው የመኪና አምራች ካምፓኒ መርሴዲስ ቤንዝ ለክሪስማሱ የመኪና ሰጦታ ና 4.5ሚሊዮን ዶላር ሎቶሪ ወጥቶሎታል በማለት እንደተለመደው አካውንቶን፣አድራሻዎንና የግል መረጃዎትን ይጠይቃሉ።
- አላማቸውና ከነሱ ራሳችንን እነዴት እንጠብቅ
አላማቸው ባብዛኛውን ጊዜ ከቻሉ የዴሊቨሪ ክፍያ ለሚሰጡት ዕቃ መጠየቅ ነው።ምክንያቱም እነሱ ከሚያቀርቡት ዕቃ ማንኛውም አይነት ክፍያ ቢሆን ትነሽ ነው ብሎ ሰውን እንዲያስብ ስለሚያደረጉት ና ህጋዊ ካምፓኒውን ለማስመሰል ብዙ ረቀት መሄዳቸው ነው።
ካልቻሉ ግን ባገኙት አጋጣሚ የክሬዲት ካርድ፣የፔይፓልና የተለያዩ የሀዋላ መላላኪያዎችን አካውንት ኢንፎርሜሽን በመውሰድ ለማጭበርበሪያ ተግባራቸው ማዋል ነው።
ከነሱ ራሳችንን እንዴት እንጠብቅ?
-በመጀመሪያ ሞባይል ቁጥራቸውን ደብል ቼክ ማድረግ
-ብዙ ጊዜ ነፃ ስጦታዎችና ሎተሪዎች እንደሚያበዙ ማወቅ
-እነሱ የሚልኩትን ሊንክ ከመጠቀም ይልቅ የዋናው ካምፓኒ ዌብሳይት ላይ በመግባት ማረጋገጥ
-በጭራሽ የግል ኢንፎርሜሽንና የአካውንት ወይም የክሬዲት ካርድ ቁጥር አለማስገባት
-ተጨማሪ ሮቴክሽን ለ ሞባይሎ ወይም ለኮምፒውተሮ መጫን