DoNotPay በተባለ የአሜሪካ ኩባንያ የበለፀገው የዓለማችን የመጀመሪያው ሮቦት ጠበቃ ከደንበኛው ጋር ፍርድ ቤት ሊቀርብ ነው፡፡
ይህ የሮቦት ሥርዓት ከፍጥነት ገደብ በላይ በማሽከርከር የተከሰሰ ደንበኛውን ነጻ ለማውጣት የሕግ ምክር ሊለግስ በቀጣዩ የካቲት ወር ፍርድ ቤት እንደሚቆም ዴይሊ ሜይል አስነብቧል፡፡
ተከሳሹ በፍርድ ቤት በሚኖረው ቆይታ የጠበቃውን ምክር ለመስማት የስማርት ስልክ መተግበሪያ እና የጆሮ ማዳመጫ እንደሚጠቀም ተገልጿል፡፡ተከሳሹ በፍርድ ቤት በሚኖረው ቆይታ የጠበቃውን ምክር ለመስማት የስማርት ስልክ መተግበሪያ እና የጆሮ ማዳመጫ እንደሚጠቀም ተገልጿል፡፡
ሮቦቱ ይህን ማድረግ የሚያስችለውን አቅም ያገኘው ተጨባጭ የሕግ እውነታዎችን መሠረት አድርጎ በመሠልጠኑ እንደሆነ ተመላክቷል፡፡
የDoNotPay ዋና ስራ አስፈፃሚ ጆሹዋ ብሮውደር በድርጅታቸው የበለፀገው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት በፍርድ ቤት በሚያደርገው ክርክር ቢሸነፍ ተከሳሹ ሊደርስበት ለሚችለው ቅጣቶች ለመካስ ቃል ገብተዋል።