ሳይንቲስቶቹ እንዳሉት የሰልካችንን መብራት በመጠቀም ማስኩ ላይ በማብራት ከኮሮና ጋር ንክኪ እንደነበረን ማወቅ ያስችላል ሲሉ ገልጸዋል።
የ ጃፓን ሳይንቲስቶች የሰሩት ይህ ማስክ የሰጎን አንቲቦዲን (ጸረ እንግዳ አካልት) በመጠቀም የተሰራ ሲሆን የአልትራቫዮሌት (UV) ብርህን ሲበራበት የኮሮና ቫይረስ ያረፈበት ቦታ በርቶ የታያል ወይም ያንጸባርቃል ። ይህም በቀላል ዋጋ ኮሮናን መመርመር የሚያስችል መሳርያ እንደሚሆን ተስፋ ተጥሎበታል።
ከዚህ በፊት የተሰሩ ምርምሮች እንዳመላከቱት ወፎች ከፍተኛ በሽታ የመከላከል አቅም አላቸው ከዚህም በመነሳት ነው ይህ ጃፓኖች የሰሩት ማስክ ላይ የሚገኘው ሽፋን (filter) ከሰጎን በተወሰደ አንቲቦዲ የተሸፈነ እንዲሆን የተደረገው።
ይህን አንቲቦዲ ለማገኘት ሳይንቲስቶቹ ጉዳት አልባ የሆነ የኮሮና ቫይረስን ለሴት ሰጎን ከሰጧት በኋል ሰጎኗ ከምትጥለው እንቁላል አስኳል ውስጥ ለኮሮና ቫይረስ የሚሆነውን አንቲቦዲ ማውጣት ችለዋል።
የሰጎኖች ሰውነት ከሌሎች የወፍ ዝርያዎች በተለየ መልኩ አንቲቦዲውን ለማምረት የሚፈጅበት ጊዜ 3ሳምንት ብቻ ነው ለምሳሌ የዶሮዎችን ሰውነት ብንወስድ ይህን አንቲቦዲ ለማምረት 12ሳምንት ይፈጅበታል እንዲሁም የሰጎን እንቁላል መጠን ትልቅ መሆን ብዙ አንቲቦዲ የሚመረትበት ቦታ እንዲኖር ያስችለዋል።
በፕሮፌሰር ያሱሂሮ ሱካሞቶ እና በክዮቶ ፕረፌክቹዋል ዩኒቨርሲቲ የተመራማሪዎች ቡድን የተሰራው ይህ ማስክ የኮሮና ቫይረስ ያለባቸው ስዎች ማስኩን እንዲያደረጉት ካደረጉ በኋላ በአፍንጫና በአፍ አካባቢ ያለው የማስኩ ገጽታ የ አልትራቫዮሌት ብርሃን ሲያርፈበት ማስኩ በርቶ (አንጸባርቆ) ታይቷል።
ሳይንቲስቶቹ እንዳሉትም የሰልካችንን መብራት በመጠቀም ማስኩ ላይ በማብራት ከኮሮና ጋር ንክኪ እንደነበረን ማወቅ ያስችላል ሲሉ ገልጸዋል።
የምርምር ቡድኑ ቀጣይ አላማ ማስኩ ላይ ተጨማሪ ጥናቶችን በማድረግ ወደፊት ምንም አይነት ብርሃን ማስኩ ላይ ማብራት ሳያስፈልግ ማስኩ በራሱ የኮሮና ቫይረስ ያረፈበት ቦታ አብርቶ እንዲያሳይ ማደረግ ነው።
“ይህ ማስክ ፒ.ሲ.አር (PCR) ከአፍንጫ ከሚወሰድ የኮሮና ምርመራ ይልቅ ቀላል የሆነ መመርመርያ ይሆናል” ያሉት የቨተርናሪ ፕሮፌሰሩ ሱካሞቶ “ ምንም ምልክት የማያሳዩ የኮሮና ታማሚዎችን በቀላሉ ለመለየት ይችላል” ብለዋል።
የፕሮፌሰር ሱካሞቶ ቡድን 32 የኮሮና ታማሚዎች ላይ 10 ቀናትን የፈጀ ሙከራ አድረገዋል ።
ቡድኑ እንዳለውም “ከሰጎን የተወሰደው አንጸባራቂ ቀለም የተደባለቀበት አንቲቦዲ በማስኩ ፊልተር (ማጣርያ ሽፋን) ላይ ይቀባል ከዚያም ስዎች ሲያስነጥሱና ሲያስሉ ቫይረሱ ማስኩ ላይ ያርፋል በመቀጠልም ከአንጸባራቂ ቀለም ጋር የተደባለቀው አንቲቦዲ እና ቫይረሱ ይገናኛሉ ከዚያም ማስኩ ላይ ብርሃን ሲበራበት ቫይረሱ ያለበት ቦታ በርቶ (አንጸባርቆ) የታያል።” ያለው ቡድኑ “ ማስኩ ላይ ብርሃን ሲበራበት ቫይረሱን ማሳየት ላይ ተሳክቶልናል “ ብለዋል ይህም ሰዎች በቀላሉ በቤታቸው ሆነው ራሳቸውን ለመመርመር ያስችላቸዋል።
ይህ ከሰጎን በተወሰደ አንቲቦዲ የተሸፈነ ማስክ ከተያዘ 8ስዓት የሆነውን አዲስ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው ላይ ጭምር ኮሮና ቫይረስ መኖሩን ማመልከት ይችላል ሲል የምርምር ቡድኑ አክሏል።
ፕሮፌሰር ሱካሞቶ በሰጎኖች ላይ ለሁለት አስርት አመታት ያክል ጥናት ያደረገ ሲሆን የሰጎኖት በርድፍሉን ፣ አለርጂዎችን እና ሌሎች በሽታዎችን የመከላከል አቅምን ለአገልግሎት ለማዋል መንገዶችን ሲያፈላልግ የነበረ ሲሆን ከዚህ በፊትም ለ ስዋይን ፍሉ (swine flu) ወረርሺኝ መመርመርያ ማስክ ሰርቶም ነበር።
ማስኩ በምያህል ዋጋ እንደሚሸጥ ባይገለጽም የምርምር ቡድኑ ግን የማስኩን ሙከራ በ150 ሰዎች ላይ በማድረግ ከመንግስት ፈቃድ አገኝቶ ለገበያ የማቅረብ አላማ እንዳለው አስታውቋል።