እነዚህ ፋብሪካ የሆኑ ሳተላይቶች ምድር ላይ ለማምረት አስችጋሪ የሆኑ ማቴሪያሎችን በህዋ ላይ ለማምረትና ምርቱ ተመርቶ ሲያልቅም ወደምድር ለማምጣት ታስበው ይሰራሉ
“ምድራችን ነገሮችን ለመስራት አስቸጋሪ ቦታ ነች” የሚለው የኤሮስፔስ ኢንጅነሩ የ አንድሪው ባኮን ኩባንያ የሆነው ስፔስ ፎርጅ (Space forge) መቀመጫውን በሃገረ እንግሊዝ ያደረገ ሲሆን ወደህዋ ተልከው መመለስ የሚችሉና በራሳቸው የሚሰሩ ፋብሪካ የሆኑ ሳተላይቶችን በመጠቀም ከፍተኛ አቅም ያላቸው ማቴሪያሎችን ለማምረት ያቀደ ሲሆን ይህም ምድር ላይ የሚኖርን የአየር ብክለት ይቀንሳል ። ኩባንያው ለመነሻ የሚሆን 10.2 ሚሊዮን ዶላር መድቧል።
ባኮን እና ተባባሪው ጆሽዋ ዌስትርን የህዋን የተለየ ተፈጥሮ ማለትም በጣም ትንሽ የሆነ የመሬት ስበት (ግራቪቲ) መኖሩን እንዲሁም ምንም የአየር ግፊት አለመኖሩን (ቫክዩም መሆኑን) እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ምድር ላይ ሊመረቱ የማይችሉ ማቴሪያሎችን ህዋ ላይ መስራት አስበዋል ።
ምድርን ያለማቋረጥ በሚዞረው አለም አቀፉ የህዋ ጣብያ (International Space station) መንኩራኩር ላይ አዳዲስ ማቴሪያሎች ማምረት መቻሉ ይታወቃል።
ለምሳሌ የ ፋይበር ኦፕቲክስ ኬብሎችን ምድር ላይ ሲመረቱ በመሬት ስበት (ግራቪቲ) እና የምድራችን አየር የተበከለ በመሆኑ ምክንያት ኬብሎቹ ደብዛዛ (ደመናማ) ገጸታ ያላቸው ሲሆን ህዋ ላይ ሲመረቱ ግን ጥርት ያለ ገጽታ ይኖራቸዋል።
ባኮን ሲናገርም” የፋይበር ኦፕቲክስ ኬብሎች መረጃን በፍጥነት የሚያስተላልፉ በመሆናቸው አንዱ ኪሎ 60 ሚልዮን ዶላር ዋጋ ያወጣል ሰለዚህ እነዚህን ኬብሎች ወደ ህዋ ለመላክ የሚፈጀው በኪሎ ከ5ሺህ እስክ 10ሺህ ዶላር ብቻ ስልሆነ ከወጭ አንጻር ካየነው አዋጭ ናቸው “ብሏል።
የምድራችን አየር የተበከለ በመሆኑ የ ስሚኮንዳክተሮች ምርትም አንዱ የተፈተነ ኢንዱስትሪ ሲሆን ይህም ባእድ ነገሮች ከሰሚኮንዳክተሮች ጋር እንዲቀላቅሉ ስለሚያድርግ ነው ። በህዋ ላይ ቢመረት ግን ባእድ ነገሮችን በእጅጉ የሚቀንስ ሲሆን የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ ያደርጋቸዋል።
ባኮን ሲቅጥልም “ህዋ ላይ ባለው ቅዝቃዜ ምክንያት ለፋብሪካ የሚያስፈልጉ ማቀዝቀዣዎችን መጠቀምን ሰለሚያስቀር የሃይል ፍጆታን በ 60% መቀነስ ያስችላል” ብሏል።
አየር በመኖሩ ምክንያት ምድር ላይ ለሚከናወኑ የብረት ምርቶች ከፍተኛ ሙቀትን ወይም ከፍተኛ ቅዝቃዜ መፍጠር ፈታኝ ሰራ መሆኑ ይታወቃል ይህ ግን ህዋ ላይ ከሆነ ቀላል ነው። “ህዋ ላይ አየር ስለሌለ አንድን ብረት በከፍተኛ ድረጃ ለማሞቅ በጣም ቀላል ነው” የሚለው ባኮን “ ፋብሪካ የሆኑ ሳተላይቶችን ከጸሃይ በጣም እንዲርቁ በማድረግ ብቻ -10 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ቅዝቃዜን ማግኘት እንችላለን” ብሏል።
የብረት አሎዮችን ለመስራት አንዱ ፈተና የምድር ስበት (ግራቪቲ) ነው ይህም ክብደት ያላቸውን የብረት ቅንጣቶች እርስ በእርስ እንዳይጠጋጉ ሰለሚያደርጋቸው ነው።
በተጨማሪም ህዋ ላይ ትላልቅና ጠንካራ ነገሮች ማለትም የአውሮፕላን ተርባይኖች (Turbine) ለመስራት የሚሆኑ አዳዲስ የብረት ድብልቅ አልዮች ለማምረት የሚያስችል ሲሆን ይህም አውሮፕላኖች የነዳጅ ፍጆታቸው እንዲቀንስ ያደርጋል።
የህዋ ፋብሪካዎች በኤሌክትሪክ የሚሰሩ የመኪኖችና የአውሮፕላኖችን ባትሪ ለማምረትም ምቹ ነው ተብሏል።
የንፋስ ህይል ማመንጫ ተርባይኖች መጠናቸው ሲተልቅ የሚያመርቱት ሃይልም ይጨምራል ለዚህም ሲባል ተከፋፍለው ይመረቱና በትላልቅ ብሎኖች ተገጣጥመው እንደሚያያዙ የታወቃል ። ነገር ግን እነዚህ ማያያዣ ፕሎኖችን ህዋ ላይ የበለጠ ጠንካራ አድርጎ በማምረት የንፋስ ሃይል ማመንጫ ተርባይኖች የበለጠ ትላልቅ አድርጎ ሰርቶ በመገጣጠም ተጨማሪ ሃይልን ማመንጨት ያስቸላችዋል።
የህዋ ላይ ፋብሪካዎች ምድር ላይ ካሉ ፋብሪካዎች እንደሚለዩ ማንም የሚረዳው ሃቅ ነው ። የመጀመርያው ነገር ሰዎች ሳይሆኑ ሮቦቶች ናቸው የምርት ሂደቱን የሚያከናውኑት ይህም ምድር ላይ እንዳለ የብረት አሎይ ፋብሪካ ለሙቀት መቆጣጠር ሲባል የሚተከሉ ትላልቅ ፓምፖች እና የብረት መስመሮችን ጭመር አላስፈላጊ ናቸው ።
በአሁኑ ሰአት በትላልቅ መጠን ምርት ከመጀመር ይልቅ የኩባንያው እቅድ ለመጀመርያ የሚሆኑ ትንንሽ ሳተላይቶችን የኦቨን ያክል ሰፋት ባላቸው ፎርጅስታር ኦርቢታል በተባሉ መንኩራኩር ለመላክ ያሰበ ሲሆን ይህም ሃሳብ በሚቀጥለው አመት ይሞከራል።
እነደሚታወቀው ሳተላይቶች ወደህዋ ተልከው የአገልግሎት ጊዜያቸው ሲያበቃ እዛው ህዋ ላይ ይቀራሉ ይህም ለ ስፔስ ፎርጅ ኩባንያ ትልቅ ፈተና እንደሚሆን ይጠበቃል ምክንያቱም ፋብሪካ የሆኑት ማምረቻ ሳተላይቶች የተመረተውን ምርት መደምድር ይዘው መመለስ አለባቸውና።
ነገር ግን በቅርቡ ስፔስ አክስ እና ቨርጂን ኦርቢት የተባሉት ኩባንያዎች ሳተላይቶች ወደህዋ ደርሰው የሚመለሱበትን መንገድ ማገኘት ችለዋል።
በመጨረሻም ስፔስ ፎርጅ ኩባንያ መልሰው መጠቀም የሚቻሉ ሳተላይቶች የሚሰራበትን ቴክኖሎጂ እስካሁን ይፋ አላደረገም።