
አይቢኤም በሚያዘጋጀው የኦንላይን የሶፍትዌር ደቨሎፒንግ የክህሎት የስልጠና ኔትወርክ ውስጥ በመግባት የኮምፒውተር ፕሮግራም ስልጣናዎችን ለተከታታይ ወራት የወሰደው የ6 ዓመቱ ህጻን ካታሪያ ለትምህርቱ በነበረው ፈጣን አቀባበል እና በቤተሰቦቹ እገዛ በእድሜ ትንሹ ፕሮግራመር በመሆን አዲስ ሪከርድ አስመዝግቧል፡፡ የአይቢኤም ብሎግ ፖስት እንደዘገበው ታዳጊው ድርጅቱ በሚያዘጋጀው የኦንላይን የሶፍትዌር ደቨሎፒንግ የክህሎት የስልጠና አምስት የተለያዩ የትምህርት አይነቶችን አጠናቆ በመማር ፓይተን በተባለው የኮምፒተር ፕሮግራም የሰርተፍኬት ዲግሪ ሊያገኝ ችሏል፡፡
በየትኛውም የእድሜ ደረጃ ሊሚገኙና የኮምፒውተር ፕሮግራም ለመማር የሚፍለጉ ሰዎች በሚሰታፉበት በዚህ የአይቢኤም የትምህርት እድል ላይ የተሳተፈው ይህ ታዳጊ በተለይም የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ የትምህርት ዘርፍ ላይ ለመስራት የሚያስችለውን የኮምፒውተር ፕሮግራም እንዳጠና የአይቢኤም ብሎግ ፖስት ዘግቧል፡፡ እንግሊዝ ውስጥ በምትገኝው ኖርዝሃምፕተን የተወለደው ካታሪያ ብዙ ወራትን ወሰዶ ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ በእድሜ ትንሹ ፕሮግራመር በመሆን በጊነስ የአለም ሪከርድ ስሙ ሊመዘግብ ችሏል፡፡
ታዳጊው በቤተሰቦቹ የተደረገለት የቁሳቁስ ድጋፍ እና የተሰጠው የትምህርት እድል ለዚህ አንዳበቃው የተናገረ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም የኮዲንግ ትምህርትን እንደመዝናኛ በመውሰድ ስልጠናዎቹን ያለመሰልቸት መማሩ ለጥሩ ውጤት እንዳበቃው አስረድቷል፡፡ ሌሎች ታዳጊ ልጆች የኮምፒውተር ፕሮግራም ስልጠናዎችን በሚወስውዱበት ሰዓት ራሳቸውን እያዝናኑ ሊሚሩ እንደሚገባ የሚያስረዳው ታዳጊው ካታሪያ ወደፊትም በኮግኒቲቭ የኮምፒውቲንግ መስክ ላይ ትልልቅ ስራዎችን መስራት እንደሚፈልግ ይናገራል፡፡
በአይቢኤም የሚያዘጋጀው የ Developer Skills Network ፕሮግራም የተለያዩ የኮምፒውተር ፕሮግራም ክህሎቶች ለተማሪዎች፣ ባለሙያዎች፣ ሥራ ፈላጊዎች እና አነስተኛ ንግዶች ከመላው ዓለም ከሚገኙ መንግስታት፣ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች እና ትምህርት ቤቶች ጋር በመተባበር በነጻ የኦንላይን ስልጠናዎችን ወይም ትምህርቶችን የሚሰጥ ሲሆን ፕሮግራሞችን ተከታትሎ ለጨረሰ ሰው የምስክር ወረቀቶች እና ወሳኝ የኮምፒውተር ክህሎቶችን እንዲያገኙ የሚግዝ ነው።