ዶልፊ
ዶልፊ – ስልክ የሚያክለው ልብስ ማጠቢያ መሳሪያ ወይም ዶልፊ የእጅ መጠን ያለው መሳሪያ ሲሆን ልብስዎን በአልትራሳውንድ ቴክኖሎጂ ኃይል ያጸዳል። የዚህ መሳሪያ ሃሳብ የመጣው ጀርመናዊቷ ስራ ፈጣሪ የሆነችው ሊና ሶሊስ በጉዞ ላይ እያለች የቆሸሹ ልብሶቿን ለማጠብ ስትሞክር ችግር ያጋጥማታል። እና እሷም ይህንን ችግር የሚቀርፍ መሳርያ ሰራች። አልትራሳውንድ በሕክምና እና በትላልቅ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ ለብዙ ዓመታት በተሳካ ሁኔታ ጥቅም ላይ ውሏል፤ ነገር ግን አልትራሳውንድ ለጽዳት ስራ ላይ ሲውል ግን ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
በቅርብ ጊዜ ውስጥ የሞባይል መጠን ያለው ተንቀሳቃሽ የልብስ ማጠቢያ ማሽን እንደሚኖረኝ ሰው ቢነገረኝ ላምነው አልችልም ነበር!
ያም ሆነ ይህ፣ በጉዞዎ እና ልብስ በማጠብ ጥረቶችዎ ውስጥ እርስዎን የሚረዳ በጣም አስደናቂ የሚመስል መሳሪያ አለ። መሳሪያው የአልትራሳውንድ ቴክኖሎጂን ይጠቀማል እና ዶልፊ ተብሎ የተሰየመውም ለዶልፊኖች ምርምር እና ደህንነት ድጋፍ ለመስጠት ነው።ዶልፊ ተንቀሳቃሽ ብቻ ሳይሆን መጠኑም የስማርት ስልክ ነው። በተለይም የልብስ ማጠቢያ ማሽኖች የሚያበላሿቸውን ለስላሳ ጨርቆች ዶልፊ ለማጠብ ጥቅም ላይ ይውላል። በዶልፊ በ እጅ ማጠብ የሚለው ነገር አይሰራም።
ዶልፊ እንዲሠራ ለማድረግ የሚያስፈልግዎ የኃይል ምንጭ እና ማጠቢያ ወይም ባልዲ ወይም ማንኛውንም ውሃ ሊይዝ የሚችል ነገር ብቻ ነው። ለማጠብ ሳሙና እና ልብሳችሁን ውሃ በተሞላው የእቃ ማጠቢያ ገንዳዎ ላይ ጨምሩበት፣ ዶልፊን ያብሩት፣ ውሃው ውስጥ ያስገቡት። ከ30-40 ደቂቃዎች ውስጥ ጥሩ ንጹህ ልብሶች ይኖሩዎታል። ብቻ ይጠቡ እና ያድርቁ ሁሉም ዝግጁ ይሆናል።
እንደ ሰሪዎቹ ገለጻ፣ ዶልፊን በውኃ በተሞላ ገንዳ ውስጥ ወይም ኮንቴይነር ውስጥ ተጭኖ ከተከፈተ በኋላ በውስጡ ያለው መሣሪያ ትራንስዱሰር በመባል የሚታወቀው የኤሌክትሪክ ኃይልን ወደ ከፍተኛ ድግግሞሽ የድምፅ ሞገዶች (high-frequency soundwaves) በመቀየር በሚሊዮን የሚቆጠሩ ጥቃቅን አረፋዎችን በፈሳሹ ውስጥ ይፈጥራል።
ዶልፊ የሚሰራበት መንገድ በውሃ ውስጥ የሚጓዙ ኃይለኛ የአልትራሳውንድ ሞገዶችን በማመንጨት ከፍተኛ ግፊት ያላቸው አረፋዎችን በመፍጠር ነው። እነዚህ አረፋዎች ይኮርፋሉ፣ ቆሻሻን ለማስወገድ ሳሙናውን በጨርቁ ውስጥ የሚገፉ ትንንሽ የውሃ ጄቶች ይፈጥራሉ። በተጨማሪም ከተለመደው የልብስ ማጠቢያ ማሽን 80 እጥፍ ያነሰ ጉልበት ይጠቀማል!
ነገር ግን አሁንም የልብስ ማጠቢያ ማሽንዎን አይጣሉት። ዶልፊ በማጽዳት ላይ ውጤታማ ቢሆንም፤ በማሽን ብቻ ለሚያጥቧቸው ትላልቅ መጠን ያላቸውን ልብሶች ለማጠብ ውጤታማ አይሆንም። ዶልፊ የሚያስፈልጋችሁ እና የሚጠቅማችሁ ትንንሽ ልብስ ማጠብ በምትፈልጉበት እና በምትጓዙበት ጊዜ ትንሽ የልብስ ማጠቢያ ማሽን ሲፈልጉ ነው።
የዶልፊ ሰሪዎች በዚህ ወር የመጀመሪያዎቹን ክፍሎች ለመጀመሪያዎቹ ገዢዎች ለመላክ እና ከዚያም በመጀመሪያው ሩብ አመት ውስጥ ቅድመ-ትዕዛዞችን ለመፈጸም አቅደዋል። ዶልፊ በሁለት አማራጮች ገበያ ላይ ይመጣል፤ የመጀመሪያው 109 ዶላር ሲሆን መሳሪያው መያዥያ ያለው እና ሊተነፍስ የሚችል ማንጠልጠያን ያካተተ ነው። ሁለተኛው መሳሪያ የጉዞ ፍላጎቶችዎን ለማሟላት የታሰበ ነው። ይህ በጣም ጥሩ ይመስላል እናም ትልቅ ስኬት ሊሆን ይችላል ብዬ አስባለሁ።