እግርኳስ ጫወታ ዳኝነት ከባድ ከሚያደርጉት ነገሮች መካከል ኦፍሳይድ(offside) አንዱ ነው፡፡
የዘመኑ እግር ኳስ ጨዋታ ክፍተኛ ፍጥነትና ክህሎት እየተላበሰ በመምጣቱ በእግር ካስ ጨዋታ ወቅት ኦፍሳይድን በሰክንድ ውስጥ ለይቶ ዳኝነት መስጠት ለእግር ካስ ዳኞች እጅግ በጣም ፈታኝ እየሆነ ምጥቷል፡፡
ለዚህም ነው FIFA በእግር ኳስ ሜዳ ውስጥ የሚፈጠሩ ፈጣን ክስተቶችን በቪዲዮ መልክ በመያዝ ለምሳሌ ኦፍሳይድ ሲከሰት ቪዲዮን በማየት መዳኘት የሚያስችል Video Assistant Referee (VAR) ቴክኖሎጂን ስራ ላይ ያዋለው፡፡
በእግርካስ ጨዋታ ወቅት ሊከሰቱ የሚችሉነ የተለያዩ ቅጣቶችን ሊያስከትሉ የሚችሉ ክስተቶችን ድንገት ከሰከንድ ባነሰ ግዜ ውስጥ ዳኞች ተመልክተው ተገቢውን ዳኝነት ለመስጠት ዳኞች ጫወታውን በማስቆም በ VAR የተያዘውን ቪዲዮ በመመልከት እስፈላጊውን ውሳኔ ለመስጠት ያስችላል፡፡
ነገር ግን ኳስ በሚለቀቅበት ግዜ የተጨዋቾችን አቋቋም በመለካት ተጨዋቾች ኦፍሳይድ( offside) ይሁኑ አይሁኑ በቀላሉ መወሰን ለዳኞች በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡
ዳኞች ተጨዋቾች ኦፍሳይድ መሆናቸው ወይም አለመሆናቸው በራሳቸው መወሰን ሲቸገሩ ጨዋታውን አስቁመው VAR በመመልከት ውሳኔ ለመስጠት ይሞክራሉ፡፡
ይሄ የእግርኳስ ዳኝነት ሂደት ቢያንስ ሶስት ችግሮችን ይፈጥራል፡፡
1ኛ፡- ዳኛው ጨዋታውን አስቁመው VAR በመልከት ኦፍሳይድን ለመወሰን አንዳንዴ ረዘም ያለ ግዜ ስለሚወስዱ የተጫዎችንና የደጋፊዎችን ስሜት ያቀዘቅዛል፡፡
ለምሳሌ ባለፈው ሰሞን በጣሊያን Serie A በAS Roma እና በFC Torino በተደረገው ጫወታ ዳኛው VAR አይተው ለመወሰን 7 ደቂቃ ወስዶባቸዋል፡፡፡ ይህ ምን ያህል የጨዋታውን ስሜት እንዳቀዘቀዘው ማየት ይቻላል፡፡
2ኛ፡- ዳኞች VAR ተመልክተው ለመወሰን የቱንም ያህል ግዜ ቢወስዱ ውሳኔያቸው ፍፁም/Accurate/ አይደለም፡፡
3ኛ፡- በዚህ ዓይነት መልኩ የሚወሰዱ የቅጣት ውሳኔዎች እግርካስ ተጫዋቾችን ያለ አግባብ ሊያበሳጫቸውና የጨዋታውንም ስሜት ሊያደበዝዘው ይችላል፡፡
ለዚህም ነው ፊፋ ቢያንስ ኦፍሳይድን በፍጥነትና በብቃት ለመዳኘት የሚያስችል ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለመጠቀም የወሰነው፡፡
ይህ ቴክኖሎጂ Artificial Intelligence እና የተለያዩ ሶፈትዌሮችን በመጠቀም በጣም በአጭር ሰከንድ ኦፍሳይድን ለመዳኘት ያስችላል፡፡
ይህ ቴክኖሎጂ እንዴት ነው የሚሰራው?
ወደ አስር የሚጠጉ ካሜራዎችና የተለያዩ ሴንሰሮች ስታዲዬሙ ጣሪያ ላይ እና ስታዲዬሙ ዙሪያ ባሉ ቦታዎች ይቀመጣሉ፡፡
እነዚህ ካሜራዎችና ሴንሰሮች ኦፍሳይድ ቦታ(Position) አካባቢ በእንቅስቀሴ ላይ ያሉ ተጨዋቾችን አቋቋም(የእያንዳንዱ ተጨዋች ቅልጥም ያለበት ቦታ) በካሜራ ይይዛሉ፡፡ ዳኛው ኦፍሳይድ የተፈጠረ ከመሰለው እና እርግጠኛ ግነ መሆን ካልቻለ ጨዋታውን አስቁሞ ካሜራዎች የያዙትን ፎቶዎች በማየት በሰከንድ ውስጥ ውሳኔ መስጠት እንዲችሉ ያስችላል፡፡
ይህ ብቻ አይደለም፤ ፊፋ ስራ ላይ ያዋለው ይህ ቴክኖሎጂ ኦፍሳይድ ተፈጥሮ ነገር ግን ዳኛው ካላዩት ቴክኖሎጂው እራሱ ለዳኞች ኦፍሳይድ መፈጠሩን መልዕክት(Notification)ያስተላልፋል፡፡