fbpx

የማይክሮሶፍት የፍለጋ ድረ ገጽ ከአዳዲስ ማሻሻያዎች ጋር ይፋ ሆነ

POZNAN, POL – SEP 23, 2020: Laptop computer displaying logo of Bing, a web search engine owned and operated by Microsoft

ቢንግ ተብሎ የሚታወቀው የማይክሮሶፍት የፍለጋ ድረ ገጽ (ብራውዘር) ጊዜው ከደረሰበት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ጋር ተጣምሮ አገልግሎት ላይ እንደሚውል ታውቋል፡፡

በፍለጋ ድረ-ገጹ ላይ የተደረገው እድሳት ባሳለፍነው የአውሮፓውያኑ ዓመት መጨረሻ ወደ አገልግሎት የገባውን የቻት ጂ.ፒ.ቲ የውይይት መለዋወጫ ሮቦት (ቻትቦት) ቴክኖሎጂ ያካተተ ነው፡፡

በዚህም ሰዎች ድረ-ገጹ ላይ ለሚያስገቡት ጥያቄ መልስ ወደሚያገኙባቸው ሌሎች ድረ-ገጾች ማስፈንጠሪያ (ሊንክ) ከማስቀመጥ ባለፈ ዝርዝር መልሶችን እንደሚያቀርብ ታውቋል፡፡

ተጠቃሚዎች ጥያቄዎቻቸውን በተሻለ መልኩ ለማስተካከል ከቻትቦቱ ጋር መወያየት እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡ በተጨማሪም ከጥያቄዎቹ ዐውድ ጋር ተመሳሳይ ይዘቶችን አብሮ ያቀርባል፡፡

የማይክሮሶፍት እርምጃ በፍለጋ ድረ-ገጽ የበላይነት ይዞ ለዓመታት የቆየውን ጉግል ስጋት ላይ በመጣል በኩባንያዎቹ መካከል የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ከባድ ፉክክር መጀመሩን ያመለክታል ሲል ቢ.ቢ.ሲ ዘግቧል፡፡

About Post Author

NATIVE ASYNC