fbpx
laptop photo

ዴስክቶፕ እና ላፕቶፕን ጨምሮ ሌሎች የኤሌክትሮኒክ ግብዓቶች በሀገር ዉስጥ ሊመረት ነዉ ተባለ

ላፕቶፕ፣ ዴስክቶፕ እና ታብሌቶችን በሀገር ውስጥ ለማምረት የዲዛይን ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር አስታውቋል። ግብአቶቹ በከፊል ሀገር ውስጥ በከፊል ደግሞ ከውጭ የሚመረቱም ይሆናል ነው የተባለው።

ዲዛይኑ በሀገር ቤት መሐንዲሶች እየተሠራ ሲሆን ወደምርት ሲገባ እሴት እንደሚታከልበት እና በተመጣጣኝ ዋጋም ለገበያ እንደሚቀርብ ተነግሯል። ለዚህ ሥራ የተመደበው 8 ሚሊዮን ዶላር በጀት ሲለቀቅ ሥራው እንደሚጀመር ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ሰለሞን ሶካ ጠቅሶ ዘግቧል።

About Post Author

NATIVE ASYNC