በዚህ በመረጃ ዘመን ሁሉም ሰው የራሱ ላፕቶፕ እንዲኖረው ይፈልጋል፡፡ኮምፒውተር በተለያዩ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ሰዎች የዕለት ተዕለት ስራቸውን በተቀላጠፈና በጣም ፈጣን በሆን መልክ በመስራት ውጤታማ እንዲሆኑ ያግዛል፡:
ተማሪዎች፤ኢንጂነሮች፤ሀኪሞች፤..ወዘተ ሁሉም በየሙያውና በየዘርፉ ላፕቶፕ ሊኖረው ግድ ይላል፡፡
ነገር ግን አብዛኞቻችን ላፕቶፕ ለመግዛት ስናስብ ምን ዓይነት ላፕቶፕ መግዛት እንዳለብን ለማወቅ እንቸገራለን፡፡
ላፕቶፕ ለመግዛት ካሰባችሁ ለናንተ የሚሆነውን ላፕቶፕ እንዴት መርጣችሁ መግዛት እንደምትችሉ ቀጥሎ እነግራችኋለሁ፡፡
ባጭሩ ላፕቶፕ ስንገዛ ስለምንገዛው ላፕቶፕ ስፔስፊኬሽን በደንብ ማወቅ ይኖርብናል ወይም የሚያቅ ባለሙያ መጠየቅ ያስፈልጋል፡፡
ከነዚህ የተለያዩ ስፔስፊኬሽኖች መካከል የላፐቶፑን ፕሮሰሰር (core i3 ወይስ corei5 ወይስ core i7 ወይስ corei9) በማየት ብቻ እንዴት ለኛ የሚሆን ላፕቶፕ መግዛት እንደምንችል እናያለን(ሌላውን ሌላ ግዜ እናያለን)
ስለ ፕሮሰሰር ሲነሳ ኮር (core) ማለት የኮምፒውተሩ አእምሮ ማለት ነው፡፡የተለያዩ ስራዎች ለመስራት የሚያስችለው የኮምፒውተሩ ዋነኛ ክፍል ነው፡፡አንድ ኮር ማለት አንድ አእምሮ ማለት ነው፡፡ የኮሮች ቁጥር እየጨመረ በመጣ ቁጥር ላፕቶፑ አንድ ስራ ለመስራት የሚያስፈልገው የማሰላሰል አቅም፤ ፍጥነት እና ቅልጥፍና እየጨመረ ይሄዳል፡፡ፕሮሰሰሩ corei9 የሆነ ላፕቶፕ ከ corei5 ላፕቶፕ ጋር ሲነፃፀር corei9 በጣም ፈጣንና ከፍተኛ የማሰላሰል አቅም አለው ማለት ነው፡፡
ስለዚህ ላፕቶፕ ስትገዙ ለናንተ የሚሆነው ላፕቶፕ ስንት ኮር(core) መሆን አለበት የሚለውን ከኮምፒውተር አጠቃቀማችሁ እና እንደተሰማራችሁበት የሙያ ዘርፍ እየለየሁ ለማስቀምጥ ልሞክር
አብዛኞቻችን በላፕቶፓችን መስራት የምንፈልገው ስራዎች መሰረታዊ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
- መሰረታዊ ስራዎችን ለማከናወን
ለምሳሌ በላፕቶፓችን፡-
➊ የተለያዩ ዌብሳይቶችን ላመሰስ
❷ የኢሜል አገልግሎት ለመጠቀም
❸ ሶሻል ሚዲያ ለመጠቀም
❹ Micosofte word,excel,power point የመሳሰሉ አገልግሎቶች ለመጠቀም
❺ አንድ አንዴ ፊልም ላመየት ሊሆን ይችላል ላፕቶፕ የምንፈልገው፡፡
ከላይ እንተጠቀሱት ዓይነት መሰረታዊ ስራዎችን ለመስራት ከሆነ የምትገዙት ላፕቶፕ corei3 ቢሆን ይመረጣል፡፡ምክንያቱም corei3 ላፕቶፕ ዋጋው ቅናሽ ከመሆኑ በተጨማሪ ከፍተኛ የባትሪ አቅም ያለውና ከሁሉ በላይ ከላይ የተጠቀሱትን መሰረታዊ ስራዎችን ፈጣንና ቀልጣፋ በሆነ መልኩ መስራ ስለሚያስችል ተመራጭ ነው፡፡
- ተማሪዎች
ተማሪዎች እንደመረጡት ትምህርት ዓይነት ላፕቶፓቸውን ለተለያዩ ስራዎች ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡
ለምሳሌ፡-
➊ ተማሪዎች ለመረጡት የትምህርት ዓይነት የሚሆኑ ሶፍትዌሮች ለመጫንና ለመጠቀም
❷ ቀለል ያሉ ጌሞች ለመጫዎት
❸ ሙዚቃና ፊልም ለማጫዎት
❹ ሶሻልሚድያና የተለያዩ የኦፊስ ሶፍትዌሮችን(ዎርድ፤ኤክሴል..) ለመጠቀም
❺ የተለያዩ ዌብሳይቶችን ለማሰስ
ተማሪዎች ከላይ የተጠቀሱትን ስራዎች ለማከናወን የሚያስችል ላፕቶፕ ለመግዛት ከፈለጋችሁ corei5 ላፕቶፕ እንድትገዙ እመክራለሁ፡፡corei5 ላፕቶፕ በአንድ ግዜ ከአንድ እና ከዚያ በላይ ስራዎችን በጣም በፍጥነትና አስተማማኝ በሆነ መልኩ መስራት ያስችላል፡፡
corei5 ላፕቶፕ ከፍተኛ አቅም የሚፈልጉ እንደ Adobe Premiere Pro ያሉ ሶፍትዌሮችን ለመጠቀም የሚያስችሉ ስድስት(6) ኮሮች ስላሉት ለትምህርታችሁ የሚሆኑ ሶፍትዌሮችን በቀላሉ መጠቀም ያስችላል፡፡እንዲሁም አራት(4) ለቅልጥፍና የሚሆኑ ኮሮች ስላሉት ጌም እየተጫወተችሁ ላፕቶፑ ከጀርባ ሌላ ስራ መስራት ይችላል፡፡ በተጨማሪም corei5 ላፕቶፕ ሳይበላሽ እስከ 5 ዓመታት ሊቆይ ስለሚችል ላፕቶፑ ትምህርታችሁን ያስጨርሳችኋል፡፡
- ከፍተኛ ፕሮግራመሮች
ከፍተኛ ፕሮግራመሮች ወይም ቪዲዮ ኤዲተር ከሆናችሁ ላፕቶፓችሁ ከፍተኛ አቅም ያለው መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም የኮምፒውተር ፕሮግራም ኮድ ለማድረግ፤ቪዲዮ ኤዲት ለማድረግ እና 3D modeling ለመስራት ላፕቶፓችሁ ከፍተኛ አቅምና ቅልጥፍና ሊኖረው ይገባል፡፡
እንዲህ ዓይነት ሙያ ላይ የተሰማራችሁ ሰዎች የምትገዙት ላፕቶፕ corei9 እንዲሆን እመክራለሁ፡፡
ምክንያቱም Corei9 ላፕቶፖች ስምንት(8) የብቃት( performance) እና 8(ስምንት) የቅልጥፍና( efficiency) ኮሮች ያሉት በመሆኑ ከላይ እንተጠቀሱትና የመሳሳሉ ከፍተኛ አቅምና ቅልጥፍና የሚጠይቁ ስራዎችን ለመስራት ያስችላሉ።
4 ጌም አፍቃሪዎች( Gamers)
ኮምፒውተር ከሚሰራቸው እና ከፍተኛ አቅምና ከፍተኛ ቅልጥፍና ከሚፈልጉ ስራዎች መካከል ጌሞች ይጠቀሳሉ፡፡ስለዚህ ላፕቶፓችሁ ጌም ለመጫዎት ከሆነ የምትፈልጉት የምትገዙት ላፕቶፕ corei7 እንዲሆን እመክራሉ፡፡
ምክንያቱም Corei7 ላፕቶፕ ስምንት የብቃትና አራት የቅልጥፍና ኮሮች ያሉት በመሆኑ የትኛውንም ጌም በብቃት ለመጫዎት ያስችላል፡፡
ለማጠቃለል አዲስ ላፕቶፕ ስትገዙ ከላይ የተጠቀሱትን አራት ነጥቦች ከግንዛቤ በማስገባት ላፕቶፓችሁን እንድትገዙ እመክራለሁ፡፡