ላፕቶፕ፣ ዴስክቶፕ እና ታብሌቶችን በሀገር ውስጥ ለማምረት የዲዛይን ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር አስታውቋል። ግብአቶቹ በከፊል ሀገር ውስጥ በከፊል ደግሞ ከውጭ የሚመረቱም ይሆናል ነው የተባለው።
ዲዛይኑ በሀገር ቤት መሐንዲሶች እየተሠራ ሲሆን ወደምርት ሲገባ እሴት እንደሚታከልበት እና በተመጣጣኝ ዋጋም ለገበያ እንደሚቀርብ ተነግሯል። ለዚህ ሥራ የተመደበው 8 ሚሊዮን ዶላር በጀት ሲለቀቅ ሥራው እንደሚጀመር ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ሰለሞን ሶካ ጠቅሶ ዘግቧል።