fbpx
ሜታ አዲሱ የ ፌስቡክ ገጽታ
ሲኢኦ ማርክ ዙከርበርግ ሜታን ስያስተዋውቅ

ሜታ: ከአዲሱ የ ፌስቡክ ገጽታ ምን እንጠብቅ?

Home » Tech News » ሜታ: ከአዲሱ የ ፌስቡክ ገጽታ ምን እንጠብቅ?

የፌስቡክ አዲሱ ትኩረት በቦታና በ ጊዜ ሳንገደብ ነገሮችን ማከናወን በሚያስችለን ሜታቨርስ  ላይ ሆኗል።

ሜታ አዲሱ የ ፌስቡክ ድርጅት መጠርያ መሆኑን የድርጅቱ መስራች ማርክ ዙከርበርግ በ ኦክቶበር 28 2021 አስታውቋል። ሜታ የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ባሻገር ወይም በላይ ማለት ነው።የድርጅቱ ስም ወደ ሜታ ይቀየር እንጂ ቀድሞ በስሩ የነበሩት እንደ ኢንስታግራም፣ፌስቡክ እና ዋትስአፕ የመሳሰሉት ፕላትፎርሞች በነበሩበት ስያሜ ይቀጥላሉ።

አዲሱ ሜታ በ ሜታቨርስ ሃሳብ ላይ አተኩሮ የሰራል ።ሜታቨርስ የጋራ የሆነ ዲጂታል ምናባዊ አለም ወስጥ በመግባት ሰዎች ሶሻል ሚድያ እንዲጠቀሙ የሚያስችል ሲሆን በውስጡም ኦንላይን ጌሞች ፣ቨርችዋል ሪያሊት እና ኦውግመንትድ ሪያሊቲ የተሰኙትን ቴክኖሎጂዎች የያዘና ሰዎች በ ቨርችዋል (ዲጅታል በሆነ ምናባውዊ አለም) እንዲገናኙ ያደርጋል።

የቨርችዋል ሪያሊቲ መነጽር
የቨርችዋል ሪያሊቲ መነጽር

እስከዛሬ ከተለመዱት የ ኢንተርኔት አጠቃቅም ዘዴዎች ማለትም ጽሁፎችን ከማንበብ፣ፎቶ እና ቪዲዮዎችን በስልክ ወይም ኮምፕዩተር ስክሪን ከማየት ባለፈ መልኩ የሜታቭርስ ተጠቃሚዎች ራሳችው ዲጂታሉንና እውነታውን አለም በሚያገናኝ ሁኔታ ወስጥ በመግባት ሶሽል ሚድያን መጠቀም ያስችላችዋል።

ማርክ ሲናገርም “ በ ሜታቨርስ የምታስቧችውን ነገሮች በሙሉ ማደረግ ተችላላችሁ ለምሳሌ ከጓደኞቻቹ ጋር መሰባሰብ ፣አብሮ መስራት፣መማር፣መጫወት፣መገብያየት እንዲሁም ስልኮችና ኮምፕዩተሮች ሊስሩት ይችላሉ ብለን ከምናስበው በላይ አዳዲስ ነገሮችን እናያለን” ብሏል። “በቅርቡም በ ሆሎግራም(3ዲ በሆነ ምስል ) አማካኝነት ቢሮ ውስጥ መገኘትና ከ ጓደኛ ጋር መገናኘት የመሳሰሉትን እናያለን “ሲል አክሏል።

ሜታቨርስ በ ወደፊቱ ማህበራዊ ግንኙነት

ሜታቨርስ ስዎች ካሉበት ከየትኛውም ቦታ ሆነው በዲጂታል ምናባዊ (ቨርችዋል) አለም መገናኘት የሚችሉበትና በዚሁ ቨርችዋል አለም ውስጥ ራሳችንን በፈለግነው መልኩ መግለጽ እንችላለን። ለምሳሌ በስልካችን የድሮ ትውስታ ያላቸው ቪድዮዎችን ስናይ በሃሳብ ወደኋላ እንጓዛለን ሜታቨርስም ይህን በማሻሻል በቨርችዋል ሪያሊቲ መነጽር አማካኝነት ቪድዮውን ከማየት በበለጠ ውስጡ በመግባት በቦታው ያለን ያህል ስሜት እንዲሰማን ያደርጋል።

የራሳችንን በ በርችዋል አለም ስንገልጽ
የራሳችንን በ በርችዋል አለም ስንገልጽ

የቨርችዋል ሪያሊቲ መነጽር በማድረግ ብቻ ወደ ቨርችዋል የተቀየረ የራሳችንን ቤት እናገኛለን በዚህ ውስጥም ልብሳችንን መምረጥ የመሳሰሉ ተገባራትን በ ቨርችዋል አለም ወስጥ ላለው እኛነታችን መምረጥ እንችላለን።እንዲሁም ስዎችን መጋበዝ፣ አብሮ ማውራት፣ጌም መጫወት ፣ ቪድዮ ማየት፣የስዕል ጋለሪ መጎብኘት የሚያስችል ሲሆን ሁሉም ተሳታፊ ሰዎች የራሳችውን የቨርችዋል አለም ገጽታ (አቫታር) መምረጥ ይችላሉ።

ከዚህም በተጨማሪ በሜታቨርስ አለም ሰዎች በጋራ በመሆን ቦታዎችን መጎብኘት፣አዲስ ነገሮችን በጋራ መከወን፣የራሳቸውን የጋራ ጌም መስራትና ፓርቲ ማዘጋጀት የመሳሰሉትን ከፈለጉበት ሆነው በ ቨርችዋል መነጽር በመታገዝ ማከናወን ይችላሉ።

ሜታቨርስ በ ወደፊቱ የመዝናኛ ዘርፍ

በ ሜታቨርስ አማካኝነት ቤታችን ሆነን ጃፓን ወይም ስዊድን የሚካሄድ የሙዚቃ ኮንሰርት መታደም እንችላለን ይህም በቴሌቪዥን መስኮት ከምናየው በተለየ መልኩ በቨርችዋል መነጽር በመታገዝ በቦታው መገኘትና አጠገባችን ያሉ ሌሎች ተሳታፊዎችን እያየን እንዲሁም ጓደኛችንንም በቨርችውል አማካኘነት በመጋበዝ አብረን መታደም ያስችለናል።

በ ሜታቨርስ ሰዎች በጋራ ሲጫወቱ
በ ሜታቨርስ ሰዎች በጋራ ሲጫወቱ

በተጨማሪም በቨርችዋል አለም ወስጥ ላለው የኛ ገጽታ ልብስ እና ሌሎች መገልገያዎችን መግዛት እንዲሁም በዚሁ ቨርችዋል አለም ውስጥ ያሉ ግን ልንዳስሳቸውና ልንጠቀምባቸው የምንችል እንደ ሙዚቃ መሳርያዎች የመሳሰሉ እቃዎችን መግዛት እንችላለን።

ሜታቨርስ በወደፊቱ የቪድዮ ጌም

በሜታቨርስ አማካኝነት በቀላሉ በአካል የምንጫወታችውን እንደ ቼዝ ያሉ ጌሞችን በአካል መገናኘት ሳይኖርብን በ ሃሎግራም (3ዲ ምስል) በመከሰት በ ቨርችዋል አለም ወስጥ ሰዎች በአንድ ቦታ በመናኘት መጫወት ያስችላቸዋል።

በ ሃሎግራም ሰዎችህ ሲገናኙ
በ ሆሎግራም ሰዎች ሲከሰቱ

በተጨማሪም ሰዎች በጋራ በመሆን እንደ ቴኒስ ያሉ ጌሞችን በቨርችዋል አለም ወስጥ መጫወት ያስችላል በዚህም ከሚጫወቱት በተጨማሪ ሌሎችም በቭርችዋል በመገኘት ተመልካች መሆን ይችላሉ።

በተለይም ታዋቂውን የቪድዮ ጌም ጂቲኤን (grand theft auto) በሚታቨርስ አማካኝነት ጌሙ ውስጥ በቨርችዋል መነጽር በመግባት መጫወት ያስችላል ይህም እስክዛሬ ከተለመደው በኮምፕዩተር ስክሪን ከመጫወት የተለየ ሰሜት ይሰጣል ተብሏል።

ሜታቨስ በ ወደፊቱ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ

እስከዛሬ ከምናውቀው ስፖርታዊ እንቅስቃሴን በቪድዮ እየተከታተሉ ከመስራት በተለየ መልኩ ቨርችዋል መንጽር በመጠቀም በሜታቨርስ አማካኝነት አሰልጣኛችን በሆሎግራም (3ዲ ምስል) አጠገባችን ተገኝቶ እንቅሰቃሴን አብሮ መስራት ያስችላል።

ለምሳሌ አንድ ሰው የቦክስ ስፖርትን ለመለማመድ ቢፈልግ በሜታቨርስ አማካኝነት ለመለማመጃ የሚሆን ተጋጣሚ ከቨርችዋሉ አለም ማግኘት የችላል።ይህም አስደሳች በሆን መልኩ ከቨርችዋል ተጋጣሚው ጋር ግጥምያ ማደርግና መለማመድ ያስችለዋል።

በ ሜታቨርስ የጋራ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ
በ ሜታቨርስ የጋራ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ

ከዚህም በተጨማሪ ሜታቨርስ ብዛት ያላችው ሰዎች በአንድ ቦታ መገኘት ሳይጠበቅባቸው ከያሉበት ሆነው በ ቨርችዋል መነጽር አማካኘነት እንደ ቅርጫት ኳስ ያሉ የጋራ ጨዋታዎችን መጫወት ይችላሉ።

ሜታቨርስ በወደፊቱ የሰራ አለም ላይ

በሜታቨርስ አለም ሰዎች በአካል ቢሮዋቸው ውስጥ መገኘት ሳይኖርባቸው ካሉበት ቦታ ሆነው በቨርችዋል መነጽር በመታገዝ ስራችውን ማከናውን ያስችላቸዋል በዚህም ኮምፕዩተርን መጠቀም የግድ አያስፈልግም ኮምፕዩተር ላይ የምናገኛቸውን አገልግሎቶች በሙሉ በ ቨርችዋል መነጽራችን ላይ እናገኘዋለን።አለፍ ሲልም ሰራተኞች የቨርችዋል አለም ቢሮዋችውን በፈልጉት መልኩ ማስዋብና ማደራጀት ይችላሉ።

በ ሆሎግራም ቢሮ መገኘት
በ ሜታቨርስ በጋራ ሰራ መስራት

በተጨማሪም የስራ ባልደረቦቻችንን በዚሁ ቨርችዋል አለም ወስጥ ስለምናገኛቸው በቀላሉ ከያሉበት ቦታ ሆነው የስራ ወይይት ማድረግና ሰራችንን በጋራ መከወን ያስችለናል። ለምሳሌ አንድ አርክቴክት የሰራውን የህንጻ ዲዛይን በሜታቨርስ አማካኝነት ዲዛይኑ ምን እንደሚመስል በቨርችዋል ሪያሊቲ መነጽር በመጠቀም ህንጻው ወስጥ ደንበኞቹን በማስገባት እንዲመለከቱት ማድረግ ይችላል።

ሜታቨርስ በወደፊቱ የትምህርት አለም

እስከዛሬ ከለመድነው የትምህርት መማርያ መንገድ ማለትም ስለ አንድ ስለሚማሩት ነገር በጆሮ ከመስማትና በአይን ከማየት በበለጠ በሜታቨርስ አማካኝነት የምንማረውን ማንኛውም ነገር በቨርችዋል አለም ውስጥ አጠገባችን አድርገን ግልጽ በሆነ መልኩ መማር ያስችላል።

ለምሳሌ አንድ ሰው ስለ ፕላነቶች መማር ቢፈልግ በቨርችዋል መነጽሩ በመታገዝ ሁሉንም ፕላኔቶች አጠገቡ አምጥቶ እንደፈለገ እያዟዟረ፣እያቀረበና እያራቀ መመልከትና መማር ያስችለዋል።

በሜታቨርስ የወደፊቱ ትምህርት
በሜታቨርስ የወደፊቱ ትምህርት

ከዚህ በተጨማሪ በሜታቨርስ ሰዎች በቴሌፖርት (በጊዜና ቦታ ሳይገደቡ የፈለጉበት የመገኝት ቨርችዋል ቴክኖሎጂ) ወደ አንድ ቦታ መጓዝ ብቻም ሳይሆን በመረጡት ዘመን ወስጥ መገኘት ይችላሉ።

ለምሳሌም አንድ ሰው ስለጥንታዊ ሮም ማወቅ ቢፈልግ በቨርችዋል መነጽሩ በቦታውና በዘመኑ በመገኘት ከ1000 አመታት በፊት የነበሩ የሮም ጎዳናዎች ላይ ቆሞ ህንጻዎችን ሰዎችን እንዲሁም በጊዜው የነብረውን አኗኗር በሙሉ መቃኘትና ምን ይመስል እንደነበር መረዳት ያስችለዋል።

ተደጋጋሚ ልምምድን የሚጠይቁ እንደ ቀዶጥገና ያሉ ትምህርቶችህን ለመማርም በሜታቨርስ አማካኝነት በቨርችዋል አለም ወስጥ በሚገኝ ምናባዊ ታማሚ ላይ ቀዶጥገና ማድረግና ትክክለኛ ውጤት እስኪገኝ ድረስ ደጋግሞ ቀዶጥገና መለማመድ ያስችላል።

በተለይም የተግባር ልምምድ የሚጠይቁ እንደ መኪና ቴክኒሽያንነት ያሉ ስልጠናዎች በቨርችዋል አለም በተዘጋጁ የመኪና አካላት ላይ የተግባር ልምምድ ማድረግ ያስችላል።እንዲሁም ዶክዩመንታሪ ፊልሞችን ለማየት በቨርችዋል መነጽር አማካኝነት የምናየው መልከአምድር ወይም ነፍሳት አጠገብ በመገኝት በተለየ ሁኔታ መመልከት ይረዳል።

ሜታቨርስ በወደፊቱ የንግድ አለም ላይ

በሜታቨርስ ቨርችዋል አለም ውስጥ ስንኖር የሚያስፈልጉንን ቨርችዋል መገልገያዎች ልብሶች፣መልኮች ፣እቃዎች መግዛትና መሸጥ አዲሱ የቢዝነስ አማራጭ ይሆናል።ሚሊዮኖች እንደሚጠቀሙት የሚገመተው ሜታቨርስ ለ ዴቨሎፐሮችና ክርኤተሮች አዲስ የሰራ እድል ይዞ ብቅ ብሏል።

ለምሳሌ አንድ የሜታቨርስ ተጠቃሚ ግለሰብ በቨርችዋል አለም ውስጥ በሚሆንበት ጊዜ ለራሱ ገጽታ (አቫታር) አዲስ ዲጅታል መልክ ወይም ዲጅታል ልብስ ሊገበይ ያስችለዋል ።በዚህም ዴቨሎፐሮች ለዚህ ምናባዊ አለም የሚያገለግሉ አዳዳዲስ ዲጅታል ምርቶችን ፈጥሮ ለቨርችዋሉ አለም መሽጥ የችላሉ ይህም አዲስ የገቢ መንጭ እንደሚሆን የጠበቃል።

በተጨማሪም የእውነታውን አለም ምርቶችንም በቨርችዋል አለም ለማስተዋወቅና ለመሸጥ ያግዛቸዋል።

የ ቨርችዋሉ አለም ግብይት
የ ቨርችዋሉ አለም ግብይት

በመጨረሻም የ ፌስቡክ መስራች ማርክ ዙከርበርግ እንደተናገረው “ከላይ ከተዘረዘሩት በተጨማሪ ሌሎች አዳዲስ ነገሮችን ይዞ የሚመጣው ሜታቨርስ በአንድ ቨርችዋል መነጸር ብቻ በመታገዝ ከአካላዊው አለም በመውጣት ወደ አዲሱ ቨርችዋል አለም በመግባት ከዚህ በፊት ያልለመድናቸውን ነገሮች እናያለን ነገር ግን የድርጀቱ ተልእኮ ሰዎችን ከ ሰዎች ማገናኘት እንደሆነ ይቀጥላል “ብሏል።

About Post Author

NATIVE ASYNC