fbpx

ከF1 እስከ F12 ያሉት የዊንዶውስ ቁልፎች አገልግሎት

የኮምፒውተር ኪቦርዳችን ላይ ከላይ የሚገኙትን (F1-F12) በተኖች ጥቅማቸውን ያውቁ ኖሯል?

ካላወቃችሁ አትጨነቁ፡፡ ዛሬ የተወሰነ ጥቅማቸውን እናሳያችኋለን፡፡ እነዚህን የኪይቦርድ በተኖች ከዚህ በፊት ድምፅ ለመጨመር እንዲሁም የብርሃን መጠን ለማስተካከል ተጥቀምውባቸው ይሆናል፡፡ ነገር ግን ጥቅማቸው ከዚህ ከፍ ያለ ነው:: ሁሉም ኮምፒውተር በሚያስብል ሁኔታ እነዚህን በተኖች ይዞ ነው የሚመጣው፡፡ እና ምንም ማስተካከል ሳያስፈልግ መጠቀም እንችላለን፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ኮምፒውተሮች ላይ እነዚህን በተኖች ለመጠቀም FN የሚለውን በተን በቅድሚያ መንካት አለብን::

ከF1 እስከ F12 ያሉትን በተኖች ጥቅም አንድ በአንድ ከስር ዘርዝረናል …. ሼር በማድረግ ከራስዎ አልፈው ለሌሎችም ይትረፉ፡፡

🏷 በኮምፒውተራችን ኪይቦርድ ከላይ ተደርድረው
የምናገኛቸው ከF1 – F12 ያሉ ቁልፎችን Function
Key እንላቸዋለን፡፡ በዋናነትም ከሌሎች #ቁልፎች ጋር በማጣመር እንደ አቋራጭ እንጠቀምባቸዋለን፡፡ እንኘህ ቁልፎች እንደ ምንጠቀመው የ ኦፐሬቲንግ ሲስተም እና
ሶፍትዌሮች አገልግሎታቸው ይለያያል፡፡:

◽️F1
ብዙ ጊዜ የምንጠቀመው እርዳታ ስንሻ ነው፡፡ በአብዛኛው
ሶፍትዌሮች F1 ስንጫን #የ Help መስኮትን ይከፍቱልናል፡፡
ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን Start እና F1 መጫን የ
Microsoft Online Help ይከፍታል፡፡
◽️F2

የተመረጠን አይከን፤ፋይል ወይንም አቃፊ ስም ለመቀየር

F2 መጫን ይቻላል፡፡ ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን Alt

  • Ctrl + F2 መጫን #የ Open መስኮትን ይከፍታል፡፡፡
    ◽️F3
    ዴስክቶፕ ላይ ካን ስንጫን የፍላገ መስኮት ይከፈታል፡፡
    ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን ቃልን መርጠን Shift +
    F3 መጫን #የተመረጠው ቃል ውስት የሚገኙ ፊደላትን
    አንድላይ ካፒታል ወይን ስሞል ወይንም የመጀመሪያውን
    ፊደል ካፒታል ያደርግልናል፡፡
    ◽️F4
    አሁንም ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን F4 #መጫን
    ለመጨረሻ ጊዜ የተገበርነውን ይደግምልናን፡፡ ለምሳሌ
    አበበ ብለን ብንጽፍ እና F4 ብናጫን በ የምትባለውን
    ፊደለ በድጋሚ ይጽፍልናል፡፡ Alt + F4 መጫን አክቲቭ

የሆነውን መስኮት ይዘጋልናል፡፡ Ctrl + F4 ስንጫን

ደግሞ አክቲቭ ከሆነው መሰኮት ውስጥ አክቲቭ የሆነውን
ታብ ይዘጋልናል፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው በ
ብራውሰራችን ከአንደ በላይ ታብ ከከፈትን Ctrl + F4
ስንጫን ያለንበትን ታብ ብቻ ይዘጋልናለን ነገር ግን Alt +
F4 ብንጫን ሙሉ በሙሉ ብራውሰሩን ይዘጋብና ማት
ነው፡፡
◽️F5
አሁን ገበያ ላይ ባሉት አብዛኛዎ ብራውሰሮች ላይ F5
መጫን # Refresh ያደርገልና፡፡ ማይክሮሶፈት ወርድ ላይ የ
Find መስኮትን ይከፍትልናል፡፡ ማክሮሶፍት ፓወር ፖይንት
ላይ ደግሞ Slideshow ያስጀምርልና፡፡

◽️F6
በአብዛኛው ብራውሰሮች ላይ F6 ስንጫን የማውሳችን
አቅጣጫ መጠቆሚያ #(cursor) ወደ አድራሻ መጻፊያው
ይወስድልና፡፡ ከአንድ በላይ የማይከሮሶፍት ወርድ
ከከፈትን Ctrl + Shift + F6 መጫን #ወደቀጣዩ
የማይክሮሶፍት መስኮትያሸጋግረናል፡፡
◽️F7
ማይክሮሶፍት ወረድ ላይ Shift + F7 መጫን የ

Thesaurus መስኮትን ይከፍትልናል የሚያገለግለውም

ሰፔሊንግ፤ ፍቺ እና ሰዋሰው ለማስተካከል ነው፡፡
◽️F8
ኮምፒውተራችን ሲነሳ የ Windows፤ #Startup menu
ለመግባት የጠቅማል፡፡
◽️F9
በዊንዶውስ ላይ ጥቅም የለውም ነገር ግን
በማይክሮሶፍት ኦፍስ እንጠቀምበታለን

Ctrl + F9= እንዲህ አይነት ባዶ ቦታ ለማስገባት { }

ወይም የመረጥነው ቃል በዚህ ዉስጥ { } ለማስገባት
CTRL + SHIFT + F9 ሊንክ የነበረውን ሊንኩ
ለማጥፋት
◽️F10
አክቲቭ የሆነውን ዊንዶው ሜኑ ባርን አክቲቭ ለማድረግ
ያስችላል፡፡ Shift + F10 መጨን #ራይት ክሊክ
እንደማድረግ ይቆጠራል፡፡
◽️F11
በአብዛኛዎ ብርውሰሮች ላይ F10 ስንጫን
የምንመለከተው መስኮት ሙሉ በሙሉ የኮምውተራችንን
ስክሪን ይሞላዋል # (Fullscreen) ፡፡
◽️F12
ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ #የ Save as ማስኮትን
ይከፍትልናል፡፡ Ctrl + Shift + F12 ፐሪንት ያዛል፡፡

ምንጭ Muhammad Computer Technology

About Post Author

NATIVE ASYNC