ለዉጤቱ መሻሻል ዘርፉን በጥናት እና ምርምር እንዲመራ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በመንግሥት መቋቋሙ ኢትዮጵያ የተሻለ ደረጃ እንድታስመዘግብ ካስቻሏት ጉዳዮች መካከል ተብሎ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡
ኦክስፎርድ ኢንሳይትስ የተባለው አማካሪ ተቋም ዓመታዊ ሪፖርቱን ሲያዘጋጅ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን ለሕዝብ አገልግሎት በመጠቀም ረገድ የመንግሥታት ዝግጁነትን የትኩረቱ ነጥብ አድርጓል፡፡
በሪፖርቱ የመንግሥታት የዝግጁነት ሁኔታ ከሦስት አንኳር ጉዳዮች አንጻር እንደተፈተሸ ተቋሙ አስታውቋል፡፡ መንግሥት ለቴክኖሎጂው የሰጠው ትኩረት፣ የቴክኖሎጂው የፈጠራ አቅም እና በዘርፉ የተሰማራው ብቁ የሰው ኃይል እንዲሁም ዳታ እና አስፈላጊ መሠረተ ልማቶች ዝግጁነቱ የተፈተሸባቸው ተብለው ተዘርዝረዋል፡፡
የመቶ ስልሳ ሀገራትን ሁኔታ በዳሰሰው ሪፖርት ኢትዮጵያ በ2020 (እ.ኤ.አ) ከነበረችበት አስራ ሦስት ነጥቦችን በማሻሻል በመቶ አርባ ሰባተኛ ደረጃ ተቀምጣለች