እ.ኤ.አ ህዳር 17 ቀን 2024 ዓ.ም ቦታ፡ ማዶ ሆቴል፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ባሳለፍነው እሁድ ኖቬምበር 17 2024 ዓም አዲስ አበባ በሚገኘው የማዶ ሆቴል በETN Learn ፕላትፎርም አማካኝነት የተዘጋጀው የUltimate Netsa የክረምት የፎሬክስ እና የክሪፕቶከረንሲ ስልጠና ምረቃ በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የእድገት ጉዞ ውስጥ ወሳኝ የሚባል አሻራውን አሳርፎ ሊያልፍ የቻለ መርሀግብር ሊሆን ችሏል። ይህ ስልጠና ባለፉት አምስት አመታት በተለይ አገራዊ የትምህርት ስርዓታችን የጠነከረ ይዘት እንዲኖረው ከተወሰነ እና በፖሊሲ ደረጃ ፀድቆ ስራ ላይ መዋል ከጀመረ ወዲህ እየታየ ያለውን የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የመልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ የውድቀት መጠን ተገን አድርገው የመውደቅ እጣ ፈንታ ያጋጠማቸውን ኢትዮጵያዊ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች የተስፋ መቁረጥ ስሜትን ለመዋጋት የተነደፈ ሙሉ ለሙሉ በነፃ አገልግሎት ላይ የተመሰረተ ፕሮጀክት ነበር። በዚህ ከ6 ሺህ ተማሪዎች በላይ በተመዘገቡበት ስልጠና ከሁለት ወራት በላይ በሆነ ጊዜ በሶስት ሰፊ የፋይናንስ ትምህርት መስኮች ላይ ተሳትፈዋል፡
- የፎሬክስ ንግድ
- የክሪፕቶ ከረንሲ እና ብሎክቼይን ቴክኖሎጂ
- Web3.0 እና የTON ብሎክቼይን
ይህ ስነ ስርዓት የመጀመሪያውን ተመራቂ ተማሪዎችን ስኬት ሲያከብር፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የWeb3 ትምህርት እና የብሎክቼይን አጠቃቀም የወደፊት እድገት እና እጣፈንታ የማይታበል አዎንታዊ ምልክቶችን አሳይቶን ሊያልፍ ችሏል።
ዓላማ ያለው ሽርክና
ስልጠናው በአለም አቀፍ ደረጃ በመስኩ ከመሪዎቹ ተርታ ከሚመደበው የExness Limited የትሬዲንግ ፕላትፎርምጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነበር። የመዝጊያ ፕሮግራሙንም ለማድመቅ በExness የምስራቅ አፍሪካ የሽያጭ ክፍል ኃላፊ ሚስተር ኮቢ ሮስኮ በዝግጅቱ ላይ ተገኝተው ትብብሩን አፅንኦት በመስጠት፤ ስለትሬዲንግ ያላቸውን የሰፋ እውቀት ለተመራቂዎች በማካፈል እንዲሁም የተዘጋጁ ሽልማቶችን ለተማሪዎች እና ለተሸላሚዎች በማበርከት የበኩላቸውን ሊያደርጉም ችለዋል።
የተደበቀ ምስጢር፡ የETN ስነ-ምህዳር ጅማሬ
ቀለል እንዳለ የምረቃ በዓል የጀመረው መርሀግብር በኋላም በTON ብሎክቼይን ላይ የተገነባውን አብዮታዊ የብሎክቼይን እና Web3 ስነ-ምህዳር ውጤት የሆነውን የETN ስነ-ምህዳር በማስተዋወቅ እና ጠለቅ ያለ ገለፃ በመስጠት የቀጠለም ነበር።
ይህ በትውልደ ደቡብ አፍሪካዊውና ኢትዮጵያን ከልጆቿ በማይተናነስ መልኩ በሚወደው ሚስተር ጄሰን ፒተርስ አማካኝነት የተመሰረተው ይህ ስነ-ምህዳር በአምስት ዓመታት ውስጥ ከ30-50 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን ወደ TON ብሎክቼይን ለማስገባት ያለመ ነው። በመግለጫው ሂደቱም፣ ሚስተር ጄሰን ፒተርስ ይህ የአሀዱ ባች ተብሎ የተሰየመ ባች[የተማሪዎች ስብስብ] በኢትዮጵያ በብሎክቼይን ላይ የተመሰረተ የሆነውን የETN Learn የትምህርት መስጫ መድረክ የመጀመሪያ ተሳታፊዎች እና ወሳኝ አካላት እንደነበሩም አስታውቀዋል።
ሽልማቶች እና እውቅናዎች
ዝግጅቱ ተማሪዎች በተዘጋጀላቸው የትሬዲንግ ውድድር ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ሽልማት በማበርከት በእለቱ የነበረውን ድባብ የበለጠ በደስታ እንዲሞላ ሊያደርግ ችሏል። በዚህ ሂደትም ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ የወጡ ተማሪዎች የሚከተሉትን ልዩ ሽልማቶች ሊሸለሙም በቅተዋል።
- የመጀመሪያ ደረጃ፡ ላፕቶፕ
- ሁለተኛ ደረጃ፡ ታብሌት
- ሶስተኛ ደረጃ፡ ስማርት ፎን
በእለቱ ጥሪ ተደርጎላቸው በአካል የተገኙ ስልጠናውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች ሁሉ የምረቃት ሰርተፍኬት እና ከሳምንታት በፊት በ0.02 TON የተቀረጹ Soul Bound Tokens (SBTs) ሊበረከትላቸውም ችሏል። በአሃዱ ባች ምልክት የተጌጡት0 እነዚህ ቶከኖች በETN Learn ላይ ላሉት ሁሉም ኮርሶች፣ ከፍተኛ ክፍያ ያላቸውን ኮርሶችን ጨምሮ፣ እስከመጨረሻው ያለምንም ክፍያ እንዲከፍቱ የሚያደርጉ ሲሆን ይህም በተለይ ለተመራቂ ተማሪዎች ሌላ ተጨማሪ ደስታን ሊሰጣቸው ችሏል።
የETN ስነ-ምህዳር፡ ኢትዮጵያን ወደWEB3 የሚያስገባ በር
ሚስተር ጄሰን ፒተርስ በእለቱ ባደረገው ንግግር በተለየ ሁነት የETN ኮይንን ብቻ የሚጠቀሙ 13 የስነምህዳሩ[Ecosystem] አገልግሎቶችን ሰፋ ባለ ሁነት አጉልቶ አሳይቷል። የስነ-ምህዳሩን ሚና ኢትዮጵያን በዚህ መስክ አንድ ደረጃ ከፍ የሚያደርግ ተያይዞም አገሪቷን አለም ከደረሰበት የWEB3 የቴክኖሎጂ ከፍታ ላይ ለማድረስ ለአገሪቱ የዚሁ መስክ በር ሆኖ የበይነበረብ አብዮት ሊያመጣ ከጫፍ የደረሰ ፕሮጀክት መሆኑንም በገለፃው አጣቅሶ ሊያልፍ ችሏል።
በመርሀግብሩ መሳካት እውቅና ሲሰጣቸው የሚገቡ አካላት
የዚሁ ፕሮጀክት መስራች በገለፃቸው በስነ-ምህዳሩ ግንባታ ወቅት ወሳኝ ሚና ለተጫወቱ አጋሮችም የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የእውቅና ሰርተፍኬቶችም ለሚከተሉት አካላት ሊያበረክቱ ችለዋል።
- የኢትዮጵያ ብሎክቼይን ማህበር
- Endubis Wallet
- Trader Insight
- Zewd Tech
- IDENTICO
- CryptoTalk-ET
- ET Netsa Apps
ከዚሁ ጋር ተያይዞ የExness Limited ላደረገው ከፍተኛ ውለታና አስተዋፅኦ ከETN ስነምህዳር ከፍ ያለ የማስታወሻ ሽልማትም ሊበረከትለት ችሏል።
ከተማሪዎች የተደረገ የምስጋና ፕሮግራም
በመርሀግብሩ ልብን በሚነካ ሁነት፣ ተማሪዎቹ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በነፃ ላገለገሏቸው አስተማሪዎቻቸው በአሃዱ ቡድን አርማ እና ምልክት የተሰሩ የኢፖክሲ የጥበብ ስራ፤ በኢትጵያዊ ቁጥሮች ያሸበረቀ የግድግዳ ሰዓት እና ሌሎችም የፍሬም እና የሰርተፍኬት ስጦታዎችን አቅርበዋል።
የመዝጊያ ፕሮግራም
ዝግጅቱ እጅግ በጣም በሚያምር ድባብ በእራት ስነ ስርዓት ሊጠናቀቅም ችሏል። ሆኖም ግን የእለቱ አስገራሚ ሁነቶች በዚህ ያበቁ አልነበሩም። በእለቱ ለተገኙም ሆነ ከዚህ በፊት ፕሮጀክቱ በመጣበት ሂደት በነቃ ሁኔታ የተሳተፉ አባላት ያገኙት የSBT ማስታወሻ በማስታወሻነት ብቻ ከመቅረት ይልቅ በቀጣይነት እድሜልክ እስከመጨረሻው በሚኖራቸው የETN Learn ፕላትፎርም አጠቃቀም ላይ በድህረገፁ የሚቀርቡ ማናቸውም አይነት የክፍያ ትምህርታዊ ግብዓቶችን በነፃ የሚያስገኝላቸው መሆኑን የሚያበስር ቪዲዮም በቴሌግራም በይፋዊ የመማሪያ የቴሌግራም ቻናላቸው በኩል ሊገለፅላቸው ችሏል። በአጠቃላይ ለእነዚሁ አባላት 192 SBTዎች በዲጂታል መልኩ ተቀርፀው ለተማሪዎቹ ሊከፋፈሉም ችለዋል። በዚህም በዚህ ታሪካዊ እንቅስቃሴ ላይ ምናልባትም በመሰል እንቅስቃሴዎች በመሳተፍ በአገሪቷ የመጀመሪያዎቹ ተማሪዎች በመሆን ደማቅ አሻራቸውን ሊያኖሩ ችለዋል።
የወደፊት እቅድ እና እይታ
የUltimate Netsa ስልጠና እንደእውነቱ ከሆነ ከምረቃ ስነስርዓትና የትሬዲንግ እሳቤን ከማስተማርም በላይ ሆኖ አገልግሏል። በተለይ እንደአገር ኢትዮጵያ እያሳየች ካለችው የዲጂታላይዜሽን አቀባበል ዝግጅት አንፃርም ትልቅ ለውጥን እና ተስፋን የሚፈነጥቅ ፕሮጀክት መሆኑንም አስመስክሮ ሊያልፍ ችሏል። የETN ስነ-ምህዳር ኢትዮጵያን ዓለም ወደደረሰበት የWeb3 ዘመን ለማስገባት፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን በፋይናንስና ብሎክቼይን ትምህርት ለማበልፀግና ለማብቃት እንዲሁም ወደ አለም አቀፍ ዲጂታል ኢኮኖሚ እንደመሻገሪያነት ለመጠቀም ቃል ተገብቷል። ይህንን መሰሉ የነፃ አገልግሎት ላይ የተመሰረቱ ትምህርቶችን በማስቀጠልም በተለይ ኢትዮጵያውን ወጣቶች ያላቸውን እምቅ ሀይል በመጠቅም ከአለም እኩል አገራችን የምትራመድበትን ሁነት ለመፍጠር የሚያስችላቸውን ትምህርታዊ መሰረት ለመጣልም እቅዱ ግልፅ በሆነ መልኩ ሊቀመጥ ችሏል።
የአሀዱ ባች ተመራቂ ተማሪዎችም ያሳለፉትን የትምርህት ጊዜ በምርቃታችው ባጀቡበት መድረክ በኢትዮጵያም የመጀመሪያዎቹ የብሎክቼይን ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ጎህ ፈንጣቂዎች እና ፈር ቀዳጆች ሊሆኑ የቻሉበትን ታሪክ በደማቁ ፅፈው ሊያልፉ ችለዋል።