የዓለማችን የኤሌክትሮኒክስ ቆሻሻ ከታላቁ የቻይና ግንብ የበለጠ ክብደት ይኖረዋል
በ2021 የአገልግሎት ዘመናቸውን ጨርሰው እንደ ቆሻሻ የሚጣሉ የኤሌክትሮኒክስ መሳርያዎች 57 ሚሊዮን ቶን በመመዘን ከግዙፉ የቻይና ግንብ የሚበልጥ ክብደት እንደሚኖራቸው WEEE የተባለው አለም አቀፍ ተቋም አስታውቀዋል፡፡ ከአካባቢ ጥበቃ ጋር በተያያዘ ትልቅ ችግር እየሆነ በመጣው የኤሌክትሮኒክስ ወጋጅ ላይ ትኩረቱን አድርጎ የሚሰራው ዌስት ኤሌክትሪካል ኤንድ ኤሌክትሪካል ኢኩፕመንት (WEEE) የተባለው አለምአቀፍ ተቋም በፈንጆቹ 2021 ጥቅም ላይ ውሎ የሚጣለው የኤሌክትሮኒክስ ቆሻሻ እስካዘሬ ከነበረው ከፍተኛ ጭማሪ እንደሚያሳይ ግምቱን አስቀምጧል፡፡
ከዚህ በፊት በተሰሩ ጥናቶችና ትንበያዎች በየዓመቱ ከ40 እስከ 45 ሚሊዮን ቶን የሚደርስ የኤሌክትሮኒክስ መሳርያ ውጋጅ (e-waste) በአለማችን ጥቅም ላይ ውሎ ይጣል የነበረ ሲሆን ይህ አሃዝ በየዓመቱ ከፍተኛ ጭማሪ በመሳየት ላይ ይገኛል፡፡ የኤሌክትሮኒክስ መሳርያዎች የአገልግሎት ዘመናቸውን ጨርሰው እንደቆሻሻ በሚጣሉበት ጊዜ አግባብነት ያለው የአወጋገድ ስርዓት ካልተበጀላቸው አልያም ዳግም ጥቅም ላይ የሚለውሉበት ሂደት ከሌላቸው በአፈር እና በከርሰ ምድር ውሃ ላይ ጎጂ ውጤቶችን ሊያስከትሉ እንደሚችሉ የሚነገር ሲሆን ከዚህ ባለፍም በአየር ብክለት ምጣኔ ላይ የራሳቸው አስታዋፅኦ ይኖራቸዋል፡፡
በዚህ አለምአቀፍ ተቋም የተሰረው ኢዲስ ጥናት እንደሚያሳው የአገልግሎት ዘመናቸውን ጨርሰው እንደ ቆሻሻ የሚጣሉ የኤሌክትሮኒክስ መሳርያዎች መልሰው ጥቅም ላይ የሚውሉበት ሂደት ቢፈጠር ከፍተኝ ጥቅም የሚሰጡ ቢሆንም እስካሁን በአለማችን መልሶ ግልጋሎት ላይ የሚውለው የኤሌክትሮኒክስ ወጋጅ ከ20 በመቶ የማይበልጥ አይደለም፡፡ ለአብነት ከኤሌክትሮኒክስ ቆሻሻ ውስጥ በዋናነት የሚቀመጠው ስማርትፎን በቀጣዩ ምዕተ ዓመት ከፍተኛ እጥረት ይኖርባቸዋል የሚባሉትን እንደ አርሴኒክ፣ ጋሊየም፣ ታንታለም እና ካድሚየም ያሉ ግብዓቶችን ይዞ የሚገኝ ቢሆንም፤ ይህ ቁስ ዳግም ጥቅም ላይ የሚውልበት ሂደት ባለመፈጠሩ ወደፊት ከፍተኛ እጥረት ሊኖርባቸው የሚችሉ መሰል ግብዓቶችን ለማዳን አስቸጋሪ ያደርገዋል፡፡
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ግብኣቶች መልሰው ጥቅም ላይ ቢውሉ ከፍተኛ ጥቅም ቢያስገኙም፤ አሁን ባለው አሰራር የኤሌክትሮኒክስ ቆሻሻን በስፋት ጥቅም ላይ የማዋል ሁኔታ በመዋቅርም ይሁን በሰዎች የአኗኗር ሁኔታ ባለመኖሩ እነዚህ ቁሶች በአፈሮቻችን ላይ የሚለቋቸው መርዛማ ኬሚካሎች የእፅዋትን የአስተዳደግ ሂደት በመበከል እና በከርሰ ምድር ውሃ ላይ ጥፋት በማስከተል ህይወታቸውን በዚህ ላይ ለመሰረቱት የተለያዩ እንስሳት አደጋን ያመጣሉ፡፡
ይህ የስነ ምህዳር መዛባት አደጋ በእንስሳትና በእፅዋት የሚያበቃ ቢመስልም በጊዜ ሂደት በምግብ አቅርቦት ሰንሰለት እና በሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች ወደሰዎች ማምራቱ የሚቀር አይደለም፡፡ ይህን አለም አቀፍ ችግር በሚቻለው አቅም ለመቅረፍ እና የወደፊቱን የሰዎች ጤናማ ህይወት በበጎ ለማረጋገጥ አንዲህ ያሉ ቁሶች ዳግም ጥቅም ላይ የሚለውሉበት ሂደት ማበጀቱ በብዘዎች የሚደገፍ ጉዳይ ነው፡፡